"ህግን አለማወቅ ከተጠያቂነት አያድንም" በክ/...

image description
- ውስጥ Laws    0

"ህግን አለማወቅ ከተጠያቂነት አያድንም" በክ/ከተማው አስተዳደር ለሚገኙ በመንግስትና የግል ት/ቤቶች የንቃተ ህግ ክበብ ማቋቋሚያ የንቅናቄ መድረክ ተካሄደ።

የአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ አስተዳደር ፍትህ ጽ/ቤት በክ/ከተማው ለሚገኙ የመንግስትና የግል ት/ቤቶች የንቃተ ህግ ክበብ ማቋቋሚያ የንቅናቄ መድረክ አካሄዷል።

በንቅናቄው የከተማ አስተዳደሩ ፍትህ ቢሮ ምክት ኃላፊ አቶ አሰፋ መብራቴ ፣ የክ/ከተማው ፍትህ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አስናቀ ረታ፣ በ/ከተማው የዋና ስራ አስፈፃሚ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ መሀመድ አህመድ፣ ከመንግስትና ከግል ት/ቤቶች የተውጣጡ መ/ራንና ተማሪዎች እንዲሁም ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል።

በድረኩ በንቃተ ህግ ክበብ ማቋቋሚያና የሴቶችና ህፃናት ጥቃት ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሰነድን በክ/ከተማው ፍትህ ጽ/ቤት በአቃቢ ህግ ወ/ሮ ማህሌት በቀለ የክበቡ መቋቋም ዓላማ፣ አወቃቀር፣ መተዳደሪያ ደንብ እንዲሁም በሴቶችና ህፃናት አካላዊ፣ ስነ-ልቦናዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ጥቃት መጠበቅ እንደሚገባና ህጉ ዓለምአቀፋዊነት እንዳለው በሰፊ ማብራርያ ቀርቦ ከመምህራንና ተማሪዎች በጋር ውይይት ተካሄዷል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትህ ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ አሰፋ መብራቴ  በንቃንቄ መድረኩ ተገኝተው ባስተላለፉት መልዕክት ተማሪዎችና መ/ራን የንቃተ ህግ መብታቸውንና ግዴታቸው በስፋት ማስገንዘብ እንደሚገባ ጠቁመው፣ የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች፣ የህዝብና መንግስት ጥቅም እንዲጠበቅ ከዚህም ባሻገር ተማሪዎች በመልካም በስነ-ምግባር እንዲታነፁ ት/ቤቶች ንቃተ ህግ ክበብ በትኩረት መስራት እንደሚገባቸው ገልፀዋል።

የአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ፍትህ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አስናቀ ረታ በበኩላቸው ንቃተ ህግን ተማሪዎችን ማስገንዘብ ትውልድ ላይ መስራት እንደሆነ ጠቁመው፣ የንቃተ ህግ ክበብ በት/ቤቶች ማቋቋም የፍትህ ትራንስፎርሜሽን አንዱ ፍኖተ ካርታ እንደሆነና የግንዛቤ ስራዎች ከዚህ በፊት በተለያዩ አግባቦች እንደተሰራ፣ መ/ራንና ተማሪዎች መሰረታዊ የህግ ዕውቀት ሊኖራቸው እንደሚገባ አመላክተዋል።

በመጨረሻም በክ/ከተማው የዋና ስራ አስፈፃሚ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ መሀመድ አህመድ በንቅናቄው መድረኩ ንግግራቸው "ህግን አለማወቅ ከተጠያቂነት አያድንም" የሚለውን መርህ ትኩት መስጠት እንደሚገባ ጠቁመው፣ መምህራንና ተማሪዎች የት/ቤቶችን ማህበረሰብና ቤተሰቦቻቸውን በህግ ፅንሰ ሀሳብ ዙሪያ መስራት እንደሚገባቸው አመላክተዋል፡፡

                   ግንቦት 02/2017 ዓ.ም(አቃቂ ቃሊቲ)


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.