
"ወርቃማው ሀሳቦቻችን በወርቃማው ሰኞ"
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትህ ቢሮ መማማርን ማዕከል ያደረገው የሰኞ ማለዳ ፕሮግራም "ወርቃማ ሀሳቦቻችን በወርቃማው ሰኞ" በሚል መሪ ቃል የሰኞ ማለዳ ፕሮግራም የተጀመረበትን 1ኛ ዓመት በማስመልከት በደማቅ ሁኔታ አከበረ፡፡በዕለቱ የቢሮው ኃላፊ የተከበሩ አቶ ተክሌ በዛብህን ጨምሮ የማኔጅመንት አባላት፣ የታክስ ይግባኝ ኮሚሽን በየደረጃው ያሉ አመራሮችና የቢሮው ሰራተኞች በተገኙበት ፕሮግራሙ ተከናውኗል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትህ ቢሮ ኃላፊ አቶ ተክሌ በዛብህ የመክፈቻ ንግግር ባደረጉበት ወቅት ሰኞ ማለዳ ከስራ በፊት የዕውቀት ሽግግር መድረክ ምርጥ ተሞክሮ የህይወት ልምድ የናሚንለዋወጥበት፣ የስራ ተነሳሽነትን የምንፈጥርበት ዝግጅት ነው በማለት ለአንደኛ አመት ክብረ-በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
በመድረኩም የቢሮው የስነ-ምግባርና የፀረ-ሙስና መከታተያ ክፍል ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ሲሳይ በፍቃዱ ስለ ተቋማዊ ባህል ምንነት እና አስፈላጊነት ዘርዘር ባለ ሁኔታ ገለፃ አድርገዋል፡፡
በወቅቱ የወርቃማው ሰኞ በአመራሩ ታምኖበት በማስጀመር ሳይቋረጥ ክትትልና ድጋፍ በማድረግ እንዲሁም ከሰራተኛው ጋር ተግባብቶ በመስራት ልዩ ልዩ ድጋፎች በማድረግ ግንባር ቀደም ሆነው ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላደረጉ ማኔጅመንት አባላት በሰራተኛው ስም እውቅና ተሰጥቷቸዋል፡፡
የቢሮው ሰራተኞችም በየደረጃው የሚገኙ አመራሮችና ሰራተኞች በአንድ አመት ጊዜ ውስጥ በተደረገው የእውቀት ሽግግር መላው የቢሮው ማህበረሰብ እርስ በርስ የሚደጋገፍበት፣ ሰፊ ዕውቀት የተገኘበት እና መሰል ተቋማዊ ባህሎችን በመውሰድ በመተግበር ረገድ አመራሩ ሊመሰገን ይገባል ብለዋል፡፡
አቶ ተክሌ በዛብህ በማጠቃለያ ንግግራቸው በከተማችን ክብርት ከንቲባ የተጀመረው ወርቃማ ሰኞ በሰራተኛው ዘንድ ያለውን እውቀትና ድልብ ልምድ መጋራት ባህል በማድረግ በቢሮ የተጀመረውን የለውጥ ግስጋሴ ለከተማዋና ለሀገር ብልጽግና ማዋል ይጠበቅብናል ብለዋል።
ግንቦት 4/2017
ፍትህ ቢሮ
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.