
በቢሮው የሰኞ ማለዳ ፕሮግራም 50ኛውን ሳምንት መርሃ ግብር አከናወነ ፡፡
ጊዜን በአግባቡ መጠቀም ለተቋም ግንባታ ስኬታማነት ትልቅ አስተዋጽኦ አለው፡፡ይህ የተገለጸው ሰኞ ማለዳ ከስራ ሰዓት በፊት በሚደረገው የዕውቀት እና ተሞክሮ ሽግግር መርሃ ግብር ላይ ሲሆን ዛሬ ማለዳ የተከበሩ አቶተክሌ በዛብህን ጨምሮ በየደረጃው ያሉ አመራሮች እና ሰራተኞች በተገኙበት ፕሮግራሙ ተከናውኗል፡፡
በመርሃ ግብሩ ውጤታማ የጊዜ አጠቃቀም በሚል ርዕስ በቢሮው የዕቅድና በጀት ዝግጅት ክትትልና ግምገማ ባለሙያ በሆኑት በአቶ ሰለሞን ታደሰ ገለጻ ቀርቧል፡፡የሰኞ ማለዳ ከስራ ሰዓት በፊት የሚከናወነው መርሃ ግብር በተከታታይነት ሳይቆራረጥ በመካሄድ ላይ የሚገኝ ዛሬ 50ኛውን ሳምንት የያዘ ሲሆን በ ቀጣይ ፕሮግራሙ ተጠናክሮ ይቀጥላል፡፡
ግንቦት 18/2017
ፍትህ ቢሮ
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.