
የኢንፎርሜሽን ኮምኒኬሽን ቴክኖሎጂ ዳይሬክቶሬት 5 ሚሊዮን የኢትዮጵያ ኮደሮች ኢንሼቲቭ በሚል ርዕስ ዙርያ ለቢሮው ዳይሬክተሮች ስልጠና ሰጠ፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትህ ቢሮ የኢንፎርሜሽን ኮምኒኬሽን ቴክኖሎጂ ዳይሬክቶሬት 5 ሚሊዮን የኢትዮጵያ ኮደሮች ኢንሼቲቭ በሚል ርዕስ ዙርያ ለቢሮው ዳይሬክተሮች ስልጠና ሰጠ፡፡
ስልጠናውን የሰጡት በቢሮው የኢንፎርሜሽን ኮምኒኬሽን ቴክኖሎጂ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት አቶ እንዳልካቸው አስረስ ሲሆኑ በኢትዮጵያ እና በተባበሩት አረብ ኢምሬትስ መንግስታት መካከል በተደረገ ስምምነት የተነደፈ የዲጂታል ክህሎት የስልጠና መርሃ ግብር ኢኒሼቲቭ መሆኑን በመግለጽ ስልጠናው ለ8 ሳምንታት የሚቆይ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
አቶ እንዳልካቸው አክለውም ስልጠናው ወጣቱ ትውልድ በዲጂታል ኢኮኖሚ ውስጥ ተሳታፊ እንዲሆኑ ፣አዲስ የስራ እድሎችን እንዲፈጥሩ እንዲሁም ሀገራችን በቴክኖሎጂ ትራንስፎርም ማድረግ እንዲቻል እና የአዲስ አበባ ስማርት ሲቲ ራዕይን ማሳካት እንዲቻል ስልጠናው አስፈልጓል ሲሉ በ2026 5 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያንን የዲጂታል ክህሎት እንዲኖራቸዉ ያስችላል ብለዋል፡፡
17/10/2017
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.