በፍልሰት ዙሪያ የተሰሩ ተግባራት ተገመገመ።

image description
- ውስጥ Laws    0

በፍልሰት ዙሪያ የተሰሩ ተግባራት ተገመገመ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትህ ቢሮ የትብብር ጥምረት ጽ/ቤት ከትብብር ጥምረቱ አባል ተቋማትና የስደት ተመላሾች ማህበራት ተወካዮች በተገኙበት የተለያዩ መንግስታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች ጋር በመተባበር በፍልሰት ጉዳዮች ዙሪያ የተሰሩ ሥራዎችን ገምግመዋል።

በግምገማው መድረክ ላይ የትብብር ጥምረት አባላት፣ የሰደት ተመላሾች ማህበራት ተወካዮች ፣ የፍሪደም ፈንድ አጋር የሆኑ ቤዛ ፖስቴሪቲ የልማት ድርጅት፣ ሲቪኤም ኢትዮጵያ ፣ሂይወት ኢትዮጵያ  ተገኝተዋል።

በአዲስ አበባ ከተማ  ፍትህ ቢሮ በሰው የመነገድ ሰውን በህገወጥ መንገድ ድንበር ማሻገር ወንጀል ተከላካይ ትብብር ጥምረት ጽ/ቤት ኃላፊ  አቶ ዮሐንስ ብርሃኑ በመክፈቻ ንግግራቸው መንግስት ወንጀሉን ለመከላከልና ህግ ለማስከበር ብሎም ተጎጂዎችንና ተጋላጮችን ለመጠበቅ ሲባል ፖሊሲ በመቅረጽ የተለያዩ የህግ ማቀፎችና የአሰራር ሥርዓት በመዘርጋት ስራዎችን እየሰራ ይገኛል።

ኃላፊው አክለው ወንጀሉ  አገራዊ ፣ አሁግራዊ እና አለምአቀፋዊ ይዘት ያለው በመሆኑ በአንድ ተቋም ብቻ መስራት ውጤታማ ስለማያደርግ መንግስታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች ጋር በመቀናጀት በርካታ ውጤታማ ስራዎች መሰራቱን ገልጸዋል። ከተመዘገቡ ለውጦች መካከል ከ100 በላይ የሆኑ የክስ መዝገቦች በወንጀሉ ዙሪያ ለህግ ተጠያቅነት መቅረቡ፣ የውጭ አገርና የአገር ዉስጥ ስራ ዕድሎች መሰፋፋት ፣ በዲጂታል አገልግሎት ሥራዎች መጀመራቸዉ ፣ የስደት ተመላሾች ማህበራት መቋቋሙ ፣ ሰፊ የውትወታ ስራዎች መሰራታቸዉ ፣ በፍልሰት ጉዳይ ላይ የሚዲያና የህዝብ ተሳትፎ መጨመሩን ፣  የአደባባይ ንቅናቄዎችና የግንዛቤ ስራዎች በስፋት መጀመራቸው ፣ የፍልሰት ጉዳይ የጋራ  አጀንዳ እየሆነ መምጣቱ  የሁሉ የጋራ ጥረት ዉጤት መሆኑ ተጠቅሷል ። 

በፍሪደም ፈንድ ድጋፍ ተደርጎ ባለፉት 4 ዓመታት ውስጥ በህገወጥ ፍልሰት ዙሪያ  በርካታ ስራዎች በጋራ መሰራታቸውን ገልጸው በሂደቱ የነበሩ ጠንካራ እና ደካማ ጎኖችን በማቅረብ በቀጣይ ትኩረት አቅጣጫዎች ላይ ምክክር ለማድረግ መድረኩን ማዘጋጀታቸውን ገልጸዋል።

በተለይም መድረኩ ያስፈለገው በተለያየ ጊዜ ከመንግስት  ጋር በመተባበርና በመደጋገፍ መደበኛ ፍልሰት ለማበረታታትና መደበኛ ያልሆነዉን ፍልሰት ለመቀነስ የተሰሩ ስራዎች ውጤታማነታቸውን ለመገምገም ነው ተብሏል ።

በወቅቱ የተገኙ የፍርደም ፈንድ አካል የሆኑ 3ቱ ድርጅቶች የሰራቸውን  ሥራ ለተሳታፊዎች አቅርበው ውይይት ተደርጎባቸው በቀጣይ ከትብብር ጥምረቱ ጋር በተጠናከረ ሁኔታ በሚሰሩ ጉዳዮች ላይ ከተሳታፊዎችም ጥያቄዎችና አስተያየት ቀርቦ ሰፋ ያለ ወይይት ተደርጓል ።

ሰኔ 19 ቀን 2017 ዓ.ም 

ፍትህ ኮሙንኬሽን ዳይሬክቶሬት


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.