
3ኛው የፍልሰት ጉዳዮች ም/ቤት መደበኛ ጉባኤ በዛሬው ዕለት ተካሄደ።
ቢሮበጉባኤው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ እና ኢንዳስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ጃንጥራር አባይ ፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትሕ ቢሮ ኃላፊ አቶ ተክሌ በዛብህ እንዲሁም የፈዴራል፣ የከተማና የክፍለ ከተሞች ከፍተኛ የመንግስት ስራ ኃላፊዎች እና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት ተወካዮች ተገኝተዋል::
የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ እና ኢንዳስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ጃንጥራር አባይ በሰው መነገድ፣ ሰውን በህገ-ወጥ መንገድ ድንበር ማሻገር ለአካላዊ፣ ስነልቦናዊ፣ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ ጉዳቶችና ለሞት ከመጋለጣቸው በተጨማሪ የሀገር ገጽታንም ከማበላሸት አኳያ ከፍተኛ አሉታዊ ተጽዕኖም አለው በማለት ዜጎች ለግዳጅ ለሥራና ለጉልበት ብዝበዛ፣ ለግዳጅ ወሲብ ንግድ፣ ለአካላዊና ሥነ- ልቦናዊ ጥቃት ብሎም ለአስከፊ የህይወት እንግልትና ሞት አደጋ የሚያጋልጣቸው ህገ-ወጥ የሰዎች ንግድ ዋነኛ ምክንያት መሆኑን ገልፀዋል።
አቶ ጃንጥራር አባይ አክለውም የህገ- ወጥ ፍልሰትን አሰከፊነት በመገንዘብ የፍልሰት ምክር ቤት በወጣው አዋጅ ቁጥር1178/2012 እና በአዲስ አበባ ደንብ ቁጥር 126/2014 መሠረት በመዲናዋ ስትራቴጂካዊ እቅድና ስልትን በመንደፍ ከባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት ጥምረት ኃይሉ የፍልሰት ወንጀልን በመከላከልና በመቆጣጠር ረገድ የበኩሉን ኃላፊነት ለመወጣት በርካታ ስራዎችን በማከናወን ላይ እንደሚገኙ ገልፀዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትሕ ቢሮ ኃላፊ አቶ ተክሌ በዛብህ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ባስተላለፉበት ወቅት አዲስ አበባ ስሟን የሚመጥን ስራ እየሰራች እንደምትገኝ ገልጸው ሕገ-ወጥ ፍልሰተኞችን በተመለከተ በተለያዩ ችግር ውስጥ ላሉ ነዋሪ ሴቶችን በነገዋ የሴቶች ተሃድሶ እና ልህቀት ማዕከል በማሰልጠን የስራ ዕድልም በማመቻቸት ተስፋ መዝራት መቻሉ በተለይ በኮሪደር ሁሉ አቀፍ ልማት ለበርካታ ወጣት ሀይል ጊዜያዊና ቋሚ የስራ ዕድል በመፍጠር ለስደት መነሻ ምክንያት የሆኑትን በመለየት ሀገራዊ ተልዕኮን በብቃት እየተወጣች ትገኛለች ብለዋል፡፡
ቢሮው በ2017 በጀት ዓመት በ6073 የነፃ የጥሪ ማዕከል ከማህበረሰቡ በአጠቃለይ የቀረቡ 280 የጥቆማ ጥሪዎች ሲሆን ከዚህ ውስጥ 6ቱ በሰው መነገድ እና ሰውን በህገ ወጥ መንገድ ድንበር ማሻገር ወንጀል ጋር በተያያዘ መረጃ፣ 153 የሕግ አስተያያት፣116 አግባቢነት የሌለው ሲሆኑ 6 በሰው መነገድ እና ሰውን በህገ ወጥ መንገድ ድንበር ማሻገር ወንጀል ጥቆማ በመሆኑ ለፖሊስ መረጃው እንዲደርስ ተደርጓል ሲሉ ገልጸዋል፡፡
ኃላፊው አክለውም በአዋጅ ቁጥር 1178/2012 ተግባራዊ መደረጉን ተከትሎ ደንብ ቁጥር 126/2014 በማውጣት የተለያዩ የሕግ ማዕቀፎችን በማዘጋጀት የአሰራር ስርዓት ተዘርግቷል ብለው፤ አዲስ አበባ የወንጀሉ መነሻ፣ መተላለፊያና መዳረሻ በመሆኗ ወንጀሉን ለመከላልና ለመቆጣጠር ከክልሎችና ከፌደራል ባለድርሻዎች እንዲሁም መንግስታትና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት ጋር በቅንጅት መስራት ያስፈልጋል በማለት አሳስበዋል፡፡
የ2017 በጀት ዓመት አፈጻጸም ሪፖርት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትህ ቢሮ በሰዉ መነገድና ሰዉን በህገወጥ መንገድ ድንበር ማሻገር ወንጀሎች ተከላካይ የትብብር ጥምረት ጽ/ቤት ኃላፊ በሆኑት በአቶ ዮሐንስ ብርሃኑ ቀርቦ ሰፊ ዉይይት ተደርጎበታል፡፡
የጉባኤው ተሳታፊዎች ላነሱት ጥያቄዎችና አስተያየቶች የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ ጃንጥራር አባይ እና የፍትሕ ቢሮ ኃላፊ አቶ ተክሌ በዛብህ ምላሽ በመስጠት ሁሉም በጋራ የተጣለባቸውን ተግባርና ኃላፊነት በአግባቡ እንዲወጡ ብሎም ተጠያቂነት ያለው አሰራር እንዲኖር ሰፊ ስራ መስራት እንደሚጠበቅባቸው እና ሁሉም ዜጋ በሰው የመነገድ ወንጀልን በመከላከል ረገድ የበኩላችንን ሃላፊነት እንወጣ ሲሉ አቅጣጫ በመስጠት ጉባኤው ተጠናቋል፡፡
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.