
ፍትህ ቢሮ ነጻ የሕግ አገልግሎት አሰራር ማኗል አተገባበር ዙሪያ ከክፍለ ከተሞች ውይይት አደረገ።
ዛሬ የ90 ቀናት እቅድ አካል በሆነው የበጎ ፈቃድ የሕግ አገልግሎት አሰጣጥ ማንዋል ዙሪያ ወደተግባር ለመግባት የሚያስችል ውይይት ተደርጓል።
በውይይቱ የፍትሕ ቢሮ ኃላፊ አቶ ተክሌ በዛብህን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ አመራሮች ፣የ11ዱም ክ/ከተሞች የፍትሕ ጽ/ቤት ኃላፊዎች እና የሕግ ስርጸትና ምክር መስጠት ዳይረክቶሬት ዳይረክተሮች ተገኝተዋል።
የቢሮ ኃላፊው በጎ ፈቃድን በተመለከተ አሰተዳደሩ ልዩ ትኩረት ሰጥቶት እየሰራ መሆኑን በመግለጽ ቢሮው ከሰኔ 5 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ጳጉሜ 5 ድረስ ልዩ እቅድ አቅዶ ወደስራ ከገባባቸው የ90 ቀናት ክረምት የልዩ ንቅናቄ እቅድ አንዱ በጎ ፊቃደኞችን በማሳተፍ ነጻ የሕግ አገልግሎት እና የሕግ ስርጸት ማስፋፋት ነው።
ኃላፊው አክለውም በጎ ፈቃደኛ የሕግ ሙያተኞች እና ምሩቃን ሕብረተሰቡን እንዲያገለግሉ ማድረግ የትራንስፎርሜሽን እቅዱን ለማሳካት አጋዥ ከመሆኑም በላይ አቅም የሌላቸውን የሕብረሰብ ክፍል መርዳት ትልቅ እርካታ ይሰጣል ብለዋል።
የፍትሕ ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ አሰፋ መብራቴ የበጎ ፈቃድ የሕግ አገልግሎት አሰጣጥ ማንዋል ሰነድ አቅርበው ሰፊ ማብራሪያ በሰጡበት ወቅት በደል የሚደርስባቸው የሕብረተሰብ ክፍሎች መብታቸው እና ግዴታቸው ምን ድረስ እንደሆነ የሕግ ምክር መስጠት በራሱ ቀላል ባለመሆኑ በትኩረት መስራት ይጠበቃል ብለዋል።
ከቤቱ ሐሳብ አስተያየት የተሰጠ ሲሆን ፕሮግራሙ ነባር እቅዶችን ለማሳካት መልካም አጋጣሚ መሆኑ ተነስቷል።
በመጨረሻም የቢሮ ኃላፊው አቶ ተክሌ በዛብህ ውይይቱ ወጥ በሆነ መንገድ ለመምራት እንዳስፈለገ ገልጸው ክፍለ ከተሞች ይህንን አጋጣሚ በመጠቀም በጎ ፈቃደኞችን እንደ አቅም በመጠቀም አሰራር ተከትለው እንዲተገብሩ አሳስበዋል።
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.