
ቢሮው የዕውቅና ፕሮግራም አካሄደ።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትሕ ቢሮ በበጀት ዓመቱ በተቋሙ በተለያዩ ዘርፎች የተሻለ አፈፃጸም ላስመዘገቡ የክ/ከተማ የፍትሕ ጽ/ቤት ሃላፊዎች ፣ ዳይሬክተሮች ፣ እንዲሁም ፈፃሚዎችን የሚያበረታታ የዕውቅና ፕሮግራም አካሄዷል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትሕ ቢሮ ሃላፊ አቶ ተክሌ በዛብህ ዕውቅናው የተሻለ አፈፃጸም ያስመዘገቡ ሰራተኞች እንዲበረታቱ እና ሌሎችም በቀጣይ የተሻለ አፈፃጸም ለማስመዝገብ እንዲጥሩ ማነሳሻ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ሁሉም ሰራተኞች በትጋት እየሰሩ እንደሚገኙ እና ለተቋሙ ከፍተኛ ውጤት እንዲበቃ የየበኩላቸውን አስተዋፅዖ አድርገዋል ያሉት ሃላፊው ሁሉም ተሸላሚ እንደሆኑ አንስተዋል፡፡
ይሁንና በዓመቱ በየዘርፉ ተመዝነው የላቀ አፈፃጸም ያስመዘገቡ ሰራተኞች ሊበረታቱ እንደሚገባ ገልጸው፣ ማበረታቻው ሁሉም ለመሰል ውጤት እንዲተጋ ማነቃቂያ ነው ብለዋል፡፡
በምዘናው በማዕከል ፈጻሚና ዳይሬክተሮች በክ/ከተማ የፍትሕ ጽ/ቤቶች በ2017 በጀት ዓመት የላቀ አፈጻጸም ላስመዘገቡ እውቅና እና ሽልማት ተሰጥቷቸዋል።
ሐምሌ 28/2017 ዓ.ም
ፍትሕ ቢሮ
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.