
ለሴት ፖለቲከኞች ህጋዊ ጥበቃ ለማድረግ የሚያስችል ምላሽ የሚሰጥ የፍትህ ስርአት ግንባታ በሚል ርዕስ ስልጠና ተሰጠ
ለሴት ፖለቲከኞች ህጋዊ ጥበቃ ለማድረግ የሚያስችል ምላሽ የሚሰጥ የፍትህ ስርአት ግንባታ በሚል ርዕስ በ(SIHA Network) እና ትምራን በጎ አድራጎት ድርጅት በጋራ በመሆን ለተለያዩ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትህ ቢሮ አመራሮች እና ፈፃሚዎች ስልጠና ተሰጠ፡፡ በለቱ ስልጠና የሰጡት ወ/ሪት ሜሮን አራጋው የኢትዮጲያ ሴት ጠበቆች ማህበር ዳይሬክተር ሲሆኑ፤ ሴቶች ወደ አመራርነት ሲመጡ እና ስልጣን ላይ በሚሆኑበት ግዜ የሚያጋጥሟቸውን የተለያዩ ተግደሮቶች እና መፍትሄዎቻቸውን ከሀገር ውስጥ ህግ እና ከተለያዩ አለም አቀፍ ህጎች አንፃር ስልጠና ሰጥተዋል፡፡ ስልጠናው የተግባር እና የቡድን ውይይቶችን ጨምሮ የያዘና ሲሆን፤ ተሳታፊዎች ሴቶች በተቋም፤ በግለሰብ እና በማህበረሰብ ወደ ፖለቲካ ሲመጡ የሚደርስባትን ተግዳሮቶች ላይ ገለፃ አድረገዋል፡፡በመጨረሻም አሰልጣኟ ከተሳታፊዎች የቀረበላትን አስተያየት እና ጥያቄ መልስ በመስጠት ስልጠናው ተጠናቋል፡፡
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.