
በህብረት ችለናል
በህብረት ችለናል
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትህ ቢሮ እና የታክስ ይግባኝ ኮሚሽን አመራሮችና ሰራተኞች የታላቁ ህዳሴ ግድባችን መጠናቀቅ ምክንያት በማድረግ ውይይት አደረጉ።
“የህዳሴ ግድባችን የኢትዮጵያ ማንሠራራት ብስራት ነው” በሚል ርዕስ በተዘጋጀ የመወያያ ሰነድ ላይ ውይይት የተደረገ ሲሆን የመድረኩን ውይይት የፍትህ ቢሮ ሀላፊ አቶ ተክሌ በዛብህ ግድባችን በርካታ ሀገራዊ፣ አህጉራዊና አለማቀፋዊ ፈተናዎች በብቃት በመሻገር ኢትዮጵያዊያንና መሪዎቿ በሕብረት መቻላችንን ያረጋገጥንበት *የታሪካችን እጥፋት ዳግማዊ አድዋ* ነው ብለዋል።
የውይይቱ ተሳታፊዎች ዝርዝር ሀሳቦች ያነሱ ሲሆን ግልፅነት ለሚፈልጉ ነጥቦች ማብራሪያ በመስጠት በማጠቃለያቸውም በተሻገረ ሕልም በላቀ ትጋት ለትውልድ የተረፈ አስተማማኝ ነገን ለመስራት ሁላችንም የበኩላችንን እንወጣ በሚል መድረኩ ተጠናቋል።
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.