
የህግ ጉዳይ ክርክር ዘርፍ የነሀሴ ወር እቅድ አፈፃፀም ገመገመ፡፡
ግምገማውን የመሩት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትሕ ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ተስፋዬ ደጀኔ ሲሆኑ የማዕከል እና የ11ዱም ክ/ከተማ የፍትሐ ብሔር እና የወንጀል ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተሮች ተገኝተዋል፡፡
አቶ ተስፋዬ ደጀኔ በመክፈቻ ንግግራቸው በደንብ ቁጥር 167 አፈጻጸም ከማህበራዊ ፍ/ቤት ከደንብ ጋር በቅንጅት ተናቦ ከመስራት አኳያ፣ የዕቅድ ዝግጅቶች ምን እንደሚመስሉ፣ የዐቃቢ ሕግ ስነ-ምግባር እንዲሁም ከሳምንታዊ የዕቅድ ሪፖርት እና በ90 ቀናት በተያያዘ አፈጻጸማችን ምን ይመስላል በሚል ውይይቱ እንደሚ ደረግ ገልጸዋል፡፡
ኃላፊው አክለውም በልዩ ትኩረት በሚሹ ጉዳዮች ማለትም በቀበሌ ቤቶች ፣ በሼዶች፣ከፕሮጀክቶች እንዴት እየመራን እንደሆነ በአጠቃላይ በዝግጅት ምዕራፍ ምን ክፍተቶች እንዳሉ የምንወያይ እንደሆነ አሳስበው አስጀምረዋል፡፡
በወቅቱ የ11ዱም ክ/ከተማ የፍትሐ ብሔር እና የወንጀል ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተሮች የነሀሴ ወር እቅድ አፈፃፀማቸውንና ያጋጠማቸውን ችግሮች በማቅረብ ትኩረት በተደረገባቸው ተግባራት ዙሪያ አቅርበው ሰፊ ውይይት ተደርጎበታል፡፡
በመጨረሻም የፍትሕ ቢሮ ፍትሐ ብሔር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ናሆም ሰለሞን እና የወንጀል ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ሙሴ አንበሴ ከቤቱ ለተነሱ ጥያቄዎች እና ሀሳቦች ምላሽ በመስጠት ተጠናቋል፡፡
መስከረም08/2018
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.