የህግ ረቂቅና ስርጸት  ዘርፍ የነሀሴ ወር እቅድ...

image description
- ውስጥ Laws    0

የህግ ረቂቅና ስርጸት  ዘርፍ የነሀሴ ወር እቅድ አፈፃፀም  ገመገመ፡፡

ግምገማውን የመሩት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትሕ ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ አሰፋ መብራቴ ሲሆኑ  የማዕከል እና የ11ዱም ክ/ከተማ  የሕግ ስርጸትና ምክር መስጠት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተሮች ተገኝተዋል፡፡

ኃላፊው አቶ አሰፋ መብራቴ ግምገማውን ባስጀመሩበት ወቅት የነሀሴ ወር አፈጻጸም ምን እንደሚመስል ፣ ከህጎች ተፈጻሚነት አኳያ የተሰሩ ስራዎች እንዲሁም የ90 ቀን እቅድ እና የትራንስፎርሜሽ እቅድ ክንውንን በተመለከተ የምንወያይበት ዕለት ነው በማለት መድረኩን  አስጀምረዋል፡፡

የነሀሴ ወር ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ያቀሩቡት ዐቃቢ  ሕግ ብዙአለም ወንድምሲሻ ሲሆኑ የከተማ አስተዳደሩን ነዋሪ እና አስፈፃሚ አካላት ንቃተ ህግ ከማሳደግ በሚመለከት  በ24 የሕግ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ በማዘጋጀት ፣በወሩ ለ9475 ሰዎች ስልጠና እንደተሰጠ፣ በሬድዮ፣ በቴሌቭዥን እንዲሁም በጋዜጣ አምድ በ 4 ፕሮግራሞች ፣በብሮሸር በ2 ርዕሰ ጉዳዮች ላይ 11,720 ኮፒ በማዘጋጀት እና በማሰራጨት፣ በአማራጭ የሶሻል ሚዲያ በ4 ፕሮግራሞች ለ94,730 ሰዎች ለከተማ አስተዳደሩ ነዋሪዎች ንቃተ-ህግ እንደተፈጠረ በሪፖርቱ ገለጻ አድርገዋል፡፡

በተጨማሪም የከተማ አስተዳደሩ ነዋሪና አስፈፃሚ አካላት የሕግ ምክር አገልግሎትን ከማሳደግ፣ የ90 ቀን እቅድ እና የትራንስፎርሜሽ እቅድ ክንውንን በሚመለከት እንዲሁም ጠንካራ  እና ደካማ ጎኖች/ያጋጠሙ ችግሮች የያዘ ሪፖርት አቅርበዋል፡፡  

በወቅቱ የክ/ከ ዳይሬክቶሬቶቹ  የነሀሴ ወር እቅድ አፈፃፀም ሪፖርት አቅርበው  ጥያቄዎችና ሃሳብ አስተያየት  ሰጥተዋል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትህ ቢሮ የሕግ ስርጸትና ምክር መስጠት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት ወ/ሪት ብርሃን ደመቀ የነሀሴ ወር ዕቅድ አፈጻጸም ጥሩ እንደነበርና በአብዛኛው  ከእቅድ በላይ እንደተሰራ በመግለጽ  ከቤቱ በተነሱት ጥያቄዎች ምላሽ በመስጠት ከንቃተ ሕግ ጋር ፣ ከበጀት አጠቃቀም፣ ከሶሻል ሚዲያ አጠቃቀም አንጻር እንዲሁም አስተዳደራዊ ውሳኔን በተመለከተ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡ 

በመጨረሻም ኃላፊው አቶ አሰፋ መብራቴ ከህጎች ተፈጻሚነት አኳያ የተሰሩ ስራዎች ጥሩ እንደነበር በመግለጽ  በቀጣይ በልዩ ትኩረት ሊሰሩ የሚገቡ ጉዳዮች ውስጥ የማህበረሰብ አቀፍ ፍትህ አገልግሎት ፣ከንቃተ ህግ አኳያ እንዲሁም  ከቴክኖሎጂ አንጻር በልዩ ትኩረት በመስጠት ስራዎች ሊሰሩ ይገባል ብለዋል፡፡

መስከረም19/2018


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.