በሴቶች  መብት  ዙርያ  የፓናል ውይይት ተካሄደ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

በሴቶች  መብት  ዙርያ  የፓናል ውይይት ተካሄደ፡፡

8በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትህ ቢሮ የሴቶች እና ሕጻናት ፎካል ፐርሰን በሴቶች መብት ዙርያ ለቢሮው  ሰራተኞች የፓናል ውይይት አካሄደ፡፡በፓናል ውይይቱ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትህ ቢሮ  ዐቃቢ ሕግ የሆኑት ወ/ሮ ብዙአለም ወንድም ሲሻ ስለ ሴቶች መብት ምንነት ፣ስለ ጾታ እና የስርአተ-ጾታን ልዩነት ፣ የሴቶች መብት በአለም አቀፍ ህጎች ብሎም በኢትዮጵያ ህጎች አንጻር እንዲሁም የሴቶች መብት መከበር ለሀገር እድገት ያለውን አስተዋጽኦ በሚል ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ሰነድ አቅርበዋል፡፡

 

ዐቃቢ ሕጓ አክለውም  ሴቶች በየትኛውም ማህበረሰብ ክፍል ውስጥ ለአድልኦ የተጋለጡ እንደሆኑ በመግለጽ ለዚህም ምክንያት የሆነው ጎጂ ልማዶች፣ ኃላ ቀር  አመለካከቶች፣ በቤተሰብ፣ በህብረተሰቡ ፣በስራ ቦታ ባሉ ምክንያት ሊሆን እንደሚችል በማንሳት እኩልነታቸውን ለማረጋገጥና ይደርስባቸው የነበረውን ተጽዕኖ ለመቅረፍ  የሴቶችን እኩልነት በተለያዩ ህጎች እውቅና መስጠት ወሳኝ ነው ብለዋል፡፡

በመጨረሻም ከተሳታፊዎች በሴቶች መብት፣በድጋፍ እርምጃ(Affirmative actions)፣ በአሰሪና ሠራተኛ አዋጅ ቁጥር 1156/2011 እንዲሁም በጋብቻ ዙርያ የተለያዩ ሃሳብ አስተያየት በማንሳት ዐቃቢ ሕጓ ምላሽ በመስጠት የፓናል ውይይቱ ተጠናቋል፡፡

መስከረም 22/201


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.