
ቢሮው የ2018 በጀት ዓመት 1ኛ ሩብ አመት ዕቅድ አፈጻጸም ገመገመ።
ግምገማው በፍትህ ቢሮ ጠቅላላ ካውንስል የተካሄደ ሲሆን በተከናወኑ አበይት ተግባራት ፣ መልካም አስተዳደርን ስራዎችን ጨምሮ የኢንሸቲብ ስራዎች አፈጻጸም በጥንካሬ እና በውስንነት የታዩ ጉዳዮች በዝርዝር ቀርበው ተገምግሟል።መድረኩን የፍትህ ቢሮ ኃላፊ አቶ ተክሌ በዛብህ የመሩት ሲሆን በሩብ አመቱ የፍትሕብሔር ክርክር ከተደረገባቸው 3,183 መዝገቦች በ748 ላይ የፍ/ቤት ውሳኔ ከተሰጠባቸው 686 መዝገቦች ለመንግስት በማስወሰን በገንዘብ ሲተመን አንድ ነጥብ ስምንት ሚሊዮንብር ፣ በአይነት፡-59 ቤቶች፣ 8 ሼዶች እና 150.7 ሄክታር መሬት የሕዝብ ጥቅም በማስጠበቅ ፣ ከውሳኔዎቹም 99.48% ማስፈጸማችን፣ በግል አቤቱታ ከቀረቡ 3050 የወንጀል መዛግብት ውስጥ 2,584 ጉዳዮች በዕርቅ እልባት ማግኘታቸው ፣ የነዋሪና አስፈፃሚ አካላት ንቃተ ሕግ ለማሳደግ በመድረክ ለ17,345 ተሳታፊዎች፣ በተለያዩ ሚዲያ አማራጮች ለ409,912 ሰዎች ንቃተ ሕግ መፍጠር መቻሉ፣ በቃል ለ566 ግለሰቦች የሕግ ምክርና አስተያየት፣ 108 የውል አስተያየት፣ 40 የውል ይረቀቅልን 3 ሕጎች ማሻሻልና 15 ሕጎችን በማርቀቅ የጸደቁትን ተደራሽ ማድረግ ከጥንካሬዎች የሚጠቀሱ እንደሆነ አንስተዋል።ይሁንና ስራዎችን ሁሉም ሰራተኛ በያገባኛል እኩል ከመንቀሳቀስ አንጻር የሚታዩ ክፍተቶች ተስተካክሎ በሁሉም ተግባራት አስተዳደሩና ነዋሪዎች ከተቋማችን የሚፈልጋቸው አገልግሎቶች በቀጣይ ሩብ አመታት በተገቢው እየተፈተሹ እንዲሔዱም በመድረኩ ግምገማ ወቅት አጽንኦት ተሰጥቶታል።
መስከረም 29/2018
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.