
ቢሮው በክረምት በጎ ፈቃድ የሕግ አገልግሎት ለሰጡ ባለሞያዎች ዕውቅና ሰጠ።
በዕውቅናው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትህ ቢሮ ኃላፊ አቶ ተክሌ በዛብህን ጨምሮ፣ በየደረጃው የሚገኙ አመራሮች ፣የአስራ አንዱም ክፍለ ከተማ የፍትሕ ጽ/ቤት ኃላፊዎች ፣ዳይሬክተሮች እንዲሁም ተግባሩ በቀጥታ የሚመለከታቸው ዓቃብያነ ሕጎች ተገኝተዋል፡፡በዕለቱ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የፍትህ ቢሮ ኃላፊ አቶ ተክሌ በዛብህ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት በማስተላለፍ የበጎ ፊቃድ አገልግሎት አገልጋዩ በነጻ የሚሰጥ የህሊና እርካታ የሚያገኝበት ቢሆን ዜጎች በቀላሉ ማግኘት የማይችሉት አገልግሎቶችን የገንዘብ ፣ የጉልበት ፣ የእውቀት ክፍተቶችን የሚሸፍን በመሆኑ ለሀገር ብልጽግና ከፍተኛ አዎንታዊ ሚና ይጫወታል። እንደ ሀገራችን ኢትዮጵያ ባለፉት ተከታታይ አመታት በክረምትም ሆነ በበጋ ወቅቶች በተለያዩ ዘርፎች ወጣቶች እየተሳተፉ በቢሊዮን ብሮች የሚገመቱ አገልግሎቶች ተደራሽ መደረጉን በመግለጽ በተመሳሳይ ሁኔታ ባሳለፍነው ክረምት የሕግ ሙያቸው በጎ ፊቃደኞች በተለያዩ ዘርፎች ተሰማርተው ለነዋሪው አገልግሎት በመስጠታቸው ለበጎ ፊቃደኞች እና ላስተባበሩ አካላት ምስጋናና እውቅና ተሰጥቷል ።የፍትሕ ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ አሰፋ መብራቴ በበኩላቸው ፍትህ ቢሮ ትኩረት ሰጥቶ የሚሰራው አንዱ የፍትህ ስርዓቱን ማዘመን ሲሆን በተሳትፎአችሁ አጋዥ ተግባራትን አድርጋችኋል ሲሉ ይህም ደግሞ በገንዘብ ቢተመን በብዙ ሚሊየኖች የሚገመት ስራ ነው በማለት ለህብረተሰባችን በማህበረሰብ አቀፍ የፍትህ አገልግሎት በመስጠት በጎ ስራ ለሰራችሁ በጎ ፈቃደኞች ምስጋናችን የላቀ ነው ብለዋል፡፡የቢሮው የሕግ ስርጸት እና ምክር መስጠት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወ/ሪት ብርሐን ደመቀ በየክ/ከተማው የተከናወኑ ስራዎችን የያዘ ሪፖርት ዘርዘር ባለ ሁኔታ አቅርበዋል፡፡የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ከሀምሌ 8 ቀን 2017 እስከ መስከረም አጋማሽ ድረስ የተካሄደ ሲሆን 151 በጎ ፊቃደኞች በመሳተፍ ነጻ የቃል እና የጽሑፍ የሕግ ምክር፣ በተለያዩ የሕግ ርዕሰ ጉዳዮች ግንዛቤ ፈጠራ ፣ የሕግ ክፍል ባላቸው ተቋማት ክትትል በማድረግ እና በመሰል አገልግሎቶች ለ1,214,656 (ለአንድ ሚሊየን ሁለት መቶ አስራ አራት ሺህ ስድስት መቶ ሀምሳ ስድስት) ነዋሪዎች በተለይም ለአረጋውያን ፣ ለአካል ጉዳተኞች፣ ለተለያዩ የህግ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው የህብረተሰብ ክፍሎች አገልግሎት መሰጠቱ ተመላክቷል፡፡ የተገኘው ውጤትን በሚመለከት የተለያዩ የህግ ግንዛቤዎች በመፈጠራቸው የሕግ ጥያቄዎቻቸውን በቀላሉ ለመፍታት እንዲችሉ ፣ ህብረተሰቡ ካለበት የፋይናንስ እጥረት አንፃር ፍትህ እንዳይጓደል ትልቅ አስተዋፅኦ ያደረገ ሲሆን ህብረተሰቡ በሚኖሩበት አካባቢ ያለምንም እንግልት፣ ድካምና ወጪ ነፃ የህግ ምክር አገልግሎት እንዲያገኙ በማስቻል የነዋሪዎችን መሰረታዊ በሆነ መልኩ መብትና ግዴታቸውን ማወቅ እንዲችሉ አድርገዋል። በመጨረሻም ከቤቱ ለተነሱት ሃሳቦችና አስተያየቶች የቢሮው ሃላፊዎች ምላሽ የሰጡ ሲሆን በጎ ፊቃደኛ ባለሙያዎች የነበራቸው ቆይታ ጥሩ እንደነበረና የተለያዩ ልምዶችን እንዳገኙና ማህበረሰብን በማገልገላቸው የህሊና እርካታ እንዳገኙ አገልግሎት በበጋው ወራትም ተናክሮ እንዲቀጥል በመግባባት መቋጫ አግኝቷል፡፡
መስከረም 28/2017
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.