
በእስረኛ አያያዝ ዙርያ ስልጠና ተሰጠ፡፡
ስልጠናው በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትህ ቢሮ ሰብዓዊ መብት ድርጊት መረሀ ግብር ማስተባበሪያ ጽ/ቤት የተዘጋጀ ሲሆን በእስረኛ አያያዝ በሚል ርዕሰ ጉዳይ በአዲስ አበባ ከተማ ለሚገኙ ፖሊሶች ተሳትፈዋል።
በዕለቱ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የፍትህ ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ተስፋዬ ደጀኔ ሲሆኑ ሰብዓዊ መብት በማስከበር ሂደት ውስጥ የፖሊስ ሚና የጎላ በመሆኑ በተለይ በእስረኞች አያያዝ ምንነት በቂ የሆነ ግንዛቤ ለመፍጠር ስልጠናው እንደተዘጋጀ በመግለጽ ፖሊስ ከሰብአዊ መብት አንጻር ሊከተሏቸው ስለሚገባቸው መርሆች ምን መሆን እንዳለባቸው በንግግራቸው ተመላክቷል፡፡
ኃላፊው አክለው የፖሊስ አካላት ህግ በማስከበር ሂደት ውስጥ ያለ አድሎእና መድሎ ስራዎች መስራት እንዳለባቸውና ወንጀል ሲፈፀም ምርመራ የማካሄድ ሂደት ዲሞክራሲያዊ እንዲሆን ለማስፈፀም የሚወጡ የወንጀል ስነ-ስርአት ህጎች መሰረት በማድረግ የሰብአዊ መብት አያያዛችንን በማሻሻል ፍትህ ማስፈን ተገቢ ነው ብለዋል።
በፍትህ ቢሮ የሰብዓዊ መብት ድርጊት መረሀ ግብር ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ኃላፊ የሆኑት አቶ ግዛው አጥናፉ በበኩላቸው ሰብዓዊ መብት ለሰው ልጅ በተፈጥሮ የተሰጠው በመሆኑ ሁሉም የሚመለከተው ይህንን ማክበር ይኖርበታል በማለት በተለይ በእስረኛ አያያዝ ዙሪያ አሁን ላይ ያለው መልካም መሆኑን ገልጸው ህግ አስከባሪ አካላት ሕግና አሰራርን ተከትሎ በመስራት የተሻለ ማድረግ ይጠበቃል ብለዋል።
ስልጠናውን የሰጡት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትህ ቢሮ ዐቃቢ ሕግ ሙሴ ባዬ ሲሆኑ ስለእስረኛና ታራሚ ምንነት እና ልዩነታቸው፣ ስለ እስረኞች አያያዝ መርሆች፣በቅበላ ወቅት እስረኞች ስላላቸው መብትና ግዴታ ፣ የጥበቃ እና ቁጥጥር አስፈላጊነት፣ልዩ አያያዝ የሚያስፈልጋቸው እስረኞች በሚል ርዕሰ ጉዳዮች ሰፋ ባለ ገለጻ አቅርበዋል፡፡
በመድረኩ ተሳታፊዎች ስልጠናው ጥሩ እንደነበር በማመስገን በርካታ ሀሳቦች ተንሸራሽሮ ምላሽና ማብራሪያ በመስጠት መድረኩ ማጠቃለያ አግኝቷል።
መስከረም 30/2018
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.