
በሀገር አቀፍ ደረጃ ለ18ኛ ጊዜ እየተከበረ ያለው ብሔራዊ የሰንደቅ ዓላማ ቀን ተከበረ ።
ሠንደቅ ዓላማችን ለኢትዮጵያ ታላቅ ከፍታ ዘመን ብስራት፤ ለብሔራዊ አንድነታችን፣ ለሉኣላዊነታችንና ለኢትዮጵያ ሕዳሴ በሚል መሪቃል የ2018 ዓ.ም 18ኛው ብሔራዊ የሰንደቅ ዓላማ ቀን ዛሬ በደማቅ ሁኔታ ተከብሯል።ጥቅምት 3 ቀን 2018 ዓ.ም በሀገር አቀፍ ደረጃ ሁሉም ተቋማት 4:30 ላይ በተመሳሳይ ሰዓት እንዲከበር የኢፌዴሪ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ማስታወቁን ተከትሎ ሁሉም የቢሮ ሰራተኞች በመሳተፍ በድምቀት ተከብሯል።የዕለቱን መክፈቻ ንግግር ያደረጉት የፍትህ ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ተስፋዬ ደጀኔ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት በማስተላፍ በየዓመቱ የሰንደቅ ዓላማ ቀን የምናከብረው በጥረታቸው፣ በላባቸውና በደማቸው ሰንደቅ ዓላማችንን ከፍ ያደረጉ የሀገር ባለውለታዎቻችንን ለማመስገን እንዲሁም የሰንደቅ ዓላማ ምንነት እና የብሔራዊ ክብር መገለጫ መሆኑን ለትውልድ ለማስተላለፍ ነው ሲሉ ገልጸዋል፡፡ኃላፊው አክለውም ሠንደቅ ዓላማችን የብዝኃነታችን፣ የእኩልነታችንና የሕብረ ብሔራዊ አንድነታችን መገለጫ በመሆኑም ቀኑ ለሠንደቅ ዓላማችን ልንሰጠው የሚገባውን ክብር እና ቃል ኪዳናችንን የምናድስበት እንዲሁም የኢትዮዽያን ከፍታ ለማረጋገጥ ሁላችንም በጋራ ቃልኪዳን የምንገባበት፣ ብሔራዊ የአርበኝነት መንፈሳችንን የምንቀሰቅስበት ታላቅ ዕለት አርገን የምናከብረው ቀን ነው ብለዋል።በመጨረሻም ሰንደቅ ዓላማ በመስቀል በተቋማት ያሉ ሁሉም አመራሮች እና ሰራተኞች ቃለ ማሃላ በመፈጸም መርሃ ግብሩ ተጠናቋል፡፡
ጥቅምት 3 ቀን 2018 ዓ.ም
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.