
በአገልግሎት አሰጣጥ መማክርት ጉባኤ ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ።
በግንዛቤ ማስጨበጫው በአገልግሎት አሰጣጥ በመማክርት ጉባኤ ምስረታ፣ ማቋቋሚያና ትግበራ ማኑዋል ለፍትሕ ቢሮ አመራሮች ፣ዳይሬክተሮች ፣ ባለድርሻ አካላት እና ሲቪክ ማህበራት ተሰጥቷል። የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የፍትህ ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ አሰፋ መብራቴ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንግስት አገልግሎት አሰጣጥ ለማሻሻልና የከተማውን የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮችን ለመፍታት እንዲሁም ጥራትና ወጪ ቆጣቢ የሆኑ አሰራሮችን ለመዘርጋት ሪፎርም ውስጥ ተገብቶ በርካታ ስራ እየተሰራ መሆኑን በመግለጽ አገልግሎት አሰጣጡን በማዘመን በዚህም ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ እንደሚገኝ በንግግራቸው ተመላክቷል፡፡ ስልጠናውን የሰጡት ከፐብሊክ ሰርቪስና ሰው ሃብት ልማት ቢሮ በመጡ የአገልግሎት አሰጣጥ ክትትልና ድጋፍ ዳይሬክቶሬት የሆኑት አቶ ክንፈ ፍቅሬ ሲሆኑ በክፍል 1 ዓላማው፣ አስፈላጊነቱ፣ለሰነድ ዝግጅት መነሻና ሁኔታዎች እንዲሁም የተፈጻሚነት ወሰን በክፍል 2 የህዝብ ተሳትፎ መሰረታዊ መርሆች በመማክርት ጉባኤ ዳሰሳ፣ የካውንስሉ አሰራር የተሞክሮ ዳሰሳ፣ የሚቋቋመው የመማክርት ጉባኤ ጠቀሜታ በክፍል 3 የመማክርት ጉባኤ አደረጃጀትና አሰራር፣ በየተቋሙ የተደራጁ የመማክርት ጉባኤ ተግባርና ኃላፊነት በሚል ርዕሰ ጉዳዮች ሰፋ ባለ ገለጻ አቅርበዋል፡፡በመጨረሻም በመድረኩ ተሳታፊዎች በርካታ ሀሳቦች ተንሸራሽሮ ምላሽና ማብራሪያ በመስጠት የመማክርት ጉባኤ ስራ አስፈጻሚ አባላትን በመምረጥ መድረኩ ማጠቃለያ አግኝቷል።
ጥቅምት 04/2018
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.