
የፍትህና መልካም አስተዳደር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሱፐርቪዥን ማካሄድ ጀመረ።
በአዲስ አበባ ከተማ ም/ቤት የፍትህና መልካም አስተዳደር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የበጀት ዓመቱን የመጀመሪያ ሱፐርቪዥን አደረገ። የቋሚ ኮሚቴው ምክትል ሰብሳቢ የተከበሩ ዶ/ር መሐመድ ገልማ ሱፐርቪዥኑ ትኩረቱን ተጠሪ ተቋማት በዝግጅት ምዕራፍ ባከናወኗቸው አበይት ተግባራት ላይ እንደሚሆን ገልጸዋል።በዚህም ቋሚ ኮሚቴው ምልከታውን በአዲስ አበባ ከተማ ፍትህ ቢሮ፣የከተማ ማስለቀቅ ይግባኝ ሰሚ ጉባኤ እንዲሁም የአዲስ አበባ ከተማ ማህበራዊ ፍ/ቤት ዳኞች አስተዳደር ጽ/ቤት በመገኘት ከዝግጅት ምዕራፍ አኳያ የተሰሩ ስራዎችን ተመልክቷል።የቋሚ ኮሚቴው ም/ሰብሳቢ የተከበሩ ዶ/ር መሐመድ ገልማ በሰጡት የቃል ግብረመልስ ተቋማት በዝግጅት ምዕራፍ በርካታ ተግባራትን መፈጸማቸውንና የፍትህ ዘርፉ ላይ ለውጦች መመዝገባቸውን በመግለጽ ይህም ለተግባር ምዕራፍ ውጤታማነት ትልቅ ድርሻ እንዳለው አብራርተዋል። በቀጣይም ቀሪ ተግባራትን በማጠናቀቅ ወደ ተግባር ምዕራፍ መገባት እንዳለበት አስገንዝበዋል ።
የህ/ግ/ኮ ዳይሬክቶሬት
5/02/2018 ዓ.ም
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.