በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ሰራተ...

image description
- ውስጥ Laws    0

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ሰራተኛ አዋጅ ቁጥር 87/2017 ዓ.ም ስልጠና ተሰጠ፡፡

ስልጠናው በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትህ በህግ ስርፀትና ምክር መስጠት ዳይሬክቶሬት የተዘጋጀ ሲሆን ከተለያዩ ሴክተር መስሪያ ቤቶች የተወጣጡ ሰራተኞች  ተሳትፈውበታል፡፡በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ሰራተኛ አዋጅ ቁጥር 87/2017 ዓ.ም የሚያካትታቸውን አጠቃላይ ይዘቶች የመንግስት መስሪያ ቤት መዋቅራዊ አደረጃጀት ፣ የደመወዝ አከፋፈል ፣ ጥቅማ ጥቅም  ፣ የደመወዝ ጭማሪ እና ማበረታቻ ስርዓት በቋሚ ሰራኛነት ለመቀጠር የሚያስችሉ ሁኔታዎች ፣ የመንግስት መረጃ አያያዝና አደረጃጀት ስለቅጥር አፈፃፀም፣ ደረጃ እድገት ፣ስለ ዝውውር እና ፈቃድ ፣የመንግስት ሰራተኞች መብት እና ግዴታ እንዲሁም የአስተዳደር የዲሲፕሊን አወሳሰድ ስለ ቅሬታ ምንነት አቀራረብና አወቃቀር ፣ስለ ቀላልና ከባድ የዲስፕሊን ቅጣት፣እርምጃ አወሳሰድ በሚሉት ርዕሰ ጉዳዮች ዙርያ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትህ ቢሮ ዐቃቢ ህግ አቶ በቃሉ ከበደ ከሰፊ ማብራርያ ጋር አቅርበዋል፡፡በመጨረሻም የስልጠናው ተሳታፊዎች የተለያዩ ጥያቄዎች አስተያየቶች እና ሃሳቦችን በማንሳት ለተነሱት ጉዳዮች ዐቃቢ ህግ አቶ በቃሉ ከበደ ምላሽ በመስጠት ስልጠናው ተጠናቋል፡፡

ጥቅምት 10/ 2018

 


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.