በተቋማት የሕግ አፈጻጸም ላይ በተደረገ ክትትል እና ድጋፍ ግኝቶች ላይ ከተቋማተት አመራሮች ጋር ውይይት ተካሄደ።
በከተማ አስተዳደራችን ተቋማት የሕግ ተፈጻሚነት፣ በአስተዳደራዊ ውሎች ሕጋዊነትእና በመመሪያ አወጣጥ ስነስረዓትን በተመለከተ ለ46 የከተማ አስተዳደሩ አስፈጻሚ አካላት በተደረገ ክትትል እና ድጋፍ ወቅት በታዩ ግኝቶች የሴክተር ተቋማት አመራሮች በተገኙበት ውይይት ተደርጓል።ውይይቱን የፍትሕ ቢሮ ምክትል የቢሮ ኃላፊ አቶ ተስፋዬ ደጀኔ የከፈቱ ሲሆን በግግራቸውም ቢሮው የከተማ አስተዳደሩ ዋና የሕግ አማካሪ ሆኖ የሚሰራ ሲሆን በዚሁ መሰረት ሴክተር መ/ቤቶች በሚከሱበትና በሚከሰሱበት ወቅት የመንግስት ና የህዝብን ጥቅም ለማስጠበቅ ሲባል ስልጣን ባለው አካል ፊት ክርክር ያደርጋል የተቋማትን የሕግ አተገባበር ይከታተላል ብለዋል።ኃላፊው አክለው ዛሬ የአስፈጻሚ አካላት የሕግ አተገባበር ምን ይመስላል ተቋማት በእውቀት እየመሩት ነው ወይስ አይደለም ምን ተግዳሮት አለ የሚለውን ለመፈተሽ የሚያስችል ኮሚቴ በማደራጀት ወደስራ መገባቱን እና በግኝቱ ላይ ዛሬ ውይይት እንደሚደረግ ገልጸዋል።በወቅቱ የሕግ ስርጸት እና ምክር መስጠት ዳይሬክቶሬት ዳሬክተር የሆኑት ወይዘሪት ብርሐን ደመቀ በሕግ ተፈጻሚነት፣ በአስተዳደራዊ ውሎች ሕጋዊነትእና በመመሪያ አወጣጥ ስነስረዓትን የከተማ አስተዳደሩ አስፈጻሚ አካላት በተደረገ ክትትል ወቅት የታዩ ግኝቶችን በዝርዝር አቅርበዋል።የፍትሕ ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ተስፋዬ ደጀኔ እና የቢሮ አማካሪ ወይዘሮ ዘርፈሽዋል ንጉሴ ከቤቱ ለተነሱ ጥያቄ እና ሃሳብአስተያየት ምላሽ በሰጡበት ወቅት አዋጆች፣ ደንቦች ፣መመሪያዎች እንዲሁም ውሎች ሕጋዊነታቸው የተጠበቀ እንዲሆን እና በእውቀት እንዲመራ ስራዎች እየተፈተሹ ድክመቶች እየታረሙ ጥንካሬዎች ደግሞ ለሌሎችም ትምርት ሆነው እንዲቀጥሉ በማድረግ በቅንጅት የሕግ የበላይነትን ማረጋገጥ ያስፈልጋል ብለዋል።በመጨረሻም በህጉ መሰረት አገልግሎት ያለመስጠት የተገልጋይ እንግልት ከማስከተል በተጨማሪ የህግ ተጠያቅነትን የሚያስከትል መሆኑን አዉቆ ተግባራዊ እንዲያደርጉ አሳስቧል።
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.