ተገልጋዮች አገልግሎት ፈልገው ይህንኑ ተግባር እንዲፈጽሙ ወደተዘጋጁ ተቋማት ሲሄዱ መብትና ግዴታቸውን አውቀው ቢሄዱ የተሻለ እንደሆነ የቂርቆስ ክፍለከተማ ፍትህ ፅህፈት ቤት ገለፀ፡፡
በፌደራል የመንግስት አስተዳደር ስነ ስርዓት አዋጅ ቁጥር 1183/2012 በየደረጃው ያሉ የማህረሰብ ክፍሎችና አደረጃጀቶች አውቀውትና በቂ ግንዛቤ ይዘው እንዲንቀሳቀሱም እየተሰራ እንደሆነም ፅህፈት ቤቱ ገልፁዋል፡፡መንግስት የአገልግሎት መስጫ ተቋማትን ዘመናዊና ለአሰራር ምቹ አገልግሎቶችም ዲጂታላይዝ እንዲሆኑ በርካታ ስራዎችን ሰርቷል፤ ደንበኞችም በተቋማቱ ለመገልገል ሲሄዱ መብትና ግዴታቸውን አውቀው ይህንንም ለማስተግበር የወጣውን አዋጅ አውቀው ይገለገሉ ዘንድ ፅህፈት ቤቱ እየሰራ ነው ብለዋል የህግ ባለሙያዋና የህግ ስርፀትና ምክር መስጠት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወይዘሮ ሚስጥረ ካሳሁን።ህብረተሰቡ በህገ መንግስቱ እና በፌዴራል አስተዳደር ስነ ስርዓት አዋጅ ቁጥር 1183/2012 የተሰጠውን መብት መጠቀም ይችሉ ዘንድም ልዩ ልዩ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኮች እየተዘጋጁ ነው ዛሬም ለህዝብ አደረጃጀቶች(ለሴት ክንፍ፣ ለወጣት ክንፍ፣ ለሴት ማህበር፣ ለወጣት ማህበር እና የዕድር አመራሮች እና አባላት መድረኩን በማመቻቸት በአዋጁ ዙሪያ ግንዛቤ እንዲኖራቸው ተደርጓል ብለዋል ወይዘሮ ሚስጥረ።
ጥቅምት 11/2018 ዓ.ም
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.