በአዋጅ ቁጥር 87/2017 ዓ.ም ስልጠና ተሰጠ፡...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

በአዋጅ ቁጥር 87/2017 ዓ.ም ስልጠና ተሰጠ፡፡

ስልጠናው በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትህ ቢሮ በሰው ሃብት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት የተዘጋጀ ሲሆን የቢሮው ዳይሬክተሮችና ሰራተኞች  ተሳትፈውበታል፡፡የስልጠናውን የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሰው ሃብት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ብርሃኑ ወ/የስ  በስልጠና ሰራተኛው መብትና ግዴታውን  የሚያውቅበት በደንብና በመመርያ የሚሰራበት ስለሆነ ሰራተኛው ስልጠናውን በትኩረት እንዲከታተል አስገንዝበዋል፡፡በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ሰራተኛ አዋጅ ቁጥር 87/2017 ዓ.ም የሚያካትታቸውን አጠቃላይ ይዘቶች  የመንግስት መስሪያ ቤት መዋቅራዊ አደረጃጀት ፣ የደመወዝ አከፋፈል ፣ ጥቅማ ጥቅም  ፣ የደመወዝ ጭማሪ እና ማበረታቻ ስርዓት በቋሚ ሰራተኛነት ለመቀጠር የሚያስችሉ ሁኔታዎች ፣ የመንግስት መረጃ አያያዝና አደረጃጀት ስለቅጥር አፈፃፀም፣ ደረጃ እድገት ፣ስለ ዝውውር እና ፈቃድ ፣የመንግስት ሰራተኞች መብት እና ግዴታ እንዲሁም የአስተዳደር የዲሲፕሊን አወሳሰድ ስለ ቅሬታ ምንነት አቀራረብና አወቃቀር ፣ስለ ቀላልና ከባድ የዲስፕሊን ቅጣት፣እርምጃ አወሳሰድ በሚሉት ርዕሰ ጉዳዮች ዙርያ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትህ ቢሮ ዐቃቢ ህግ አቶ በቃሉ ከበደ ከሰፊ ማብራርያ ጋር አቅርበዋል፡፡

ጥቅምት 13/ 2018

 


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.