በደንብ ቁጥር 180/2017 ስልጠና ተሰጠ፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትህ ቢሮ የሕግ ስርጸትና ምክር መስጠት ዳይሬክቶሬት ከአዲስ አበባ ነዋሪዎች ለተወጣጡ ህብረተሰቦች በደንብ ቁጥር 180/2017 ስልጠና ሰጠ፡፡ስልጠናውን የሰጡት የፍትህ ቢሮ ዐቃቢ ሕግ እስጢፋኖስ አበበ ሲሆኑ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የወንዞች ዳርቻ ልማት እና ብክለት መከላከል ደንብ ቁጥር 180/2017 ስልጠና ሰጥተዋል፡፡በስልጠናው የደንቡ መዉጣት አስፈላጊነት፣ ወንዞችና የወንዞች ዳርቻን ከብክለት ለመከላከል እንዲቻል የተከለከሉ ተግባራት፣ ደንቡ ከማስፈጸም አኳያ የተቋማት ሃላፊነት እንዲሁም የደንቡን መተላለፍ ስለሚያስከትለዉ ዉጤት በሰፊው ገለጻ አድርገዋል፡፡ዐቃቢ ሕጉ አክለውም ሰዎች ንጹህና ጤናማ አካባቢ የመኖር መብት እንዳላቸው በመግለጽ ከመኖሪያ ቤት፣ ከአገልግሎት ሰጪ ተቋማት እና አምራች ድርጅቶች የሚወጡ ተረፈ ምርቶች፣ የግንባታና የህንጻ ፍርስራሾች፣ ደረቅ ቆሻሻ እና ሌሎች ተመሳሳይነት ያላቸው በካዮች ወደ ወንዝና በወንዝ ዳርቻ መድፋት ወይም መጣል፣ ማንኛውንም ሰው ፈቃድ ሳይሰጠው የታከመ ፍሳሽን ወደ ወንዝ መልቀቅ፤ በወንዝና በወንዝ ዳርቻ ክልል ውስጥ መጸዳዳት እና ሌሎች በደንብ ቁጥር 180/2017 በአን 7 (1)-(14) በተዘረዘሩት የተከለከሉ ተግባራት ማብራሪያ በመስጠት ደንቡ ከማስፈጸም አኳያ የተቋማት ሃላፊነት እንዲሁም የደንቡን መተላለፍ ስለሚያስከትለዉ ዉጤት ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡በመጨረሻም ከተሳታፊዎች በተነሳው ጥያቄዎች ዐቃቢ ሕጉ ምላሽ በመስጠት ተጠናቋል፡፡
14/02/2018
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.