የህግ ጉዳይ ክርክር ዘርፍ የ2018 በጀት ዓመት...

image description
- ውስጥ Laws    0

የህግ ጉዳይ ክርክር ዘርፍ የ2018 በጀት ዓመት 1ኛ ሩብ አመት እቅድ አፈፃፀም ገመገመ፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትህ ቢሮ የህግ ጉዳይ ክርክር ዘርፍ የ2018 በጀት ዓመት 1ኛ ሩብ አመት እቅድ አፈፃፀም ገመገመ፡፡ ግምገማውን የመሩት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትሕ ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ተስፋዬ ደጀኔ ሲሆኑ የ11ዱም ክ/ከተማ የፍትሐ ብሔር እና የወንጀል ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ተገኝተዋል፡፡የቢሮው ምክትል ኃላፊ አቶ ተስፋዬ ደጀኔ በመክፈቻ ንግግራቸው የ2018 በጀት ዓመት 1ኛ ሩብ አመት እቅድ አፈፃፀም ከወንጀል ጋር ተያይዞ በእርቅ ከመጨረስ አኳያ እንዲሁም ከፍትሐ- ብሔር ክርክር አኳያ ምን እንደሚመስል እና ያጋጠሙ ችግሮች ምን እንደሆኑ በተለይ ልዩ ትኩረትበሚሹ ጉዳዮች በሚመለከት በኮንሰትራክሽን ሜጋ ፕሮጀክቶች ፣ከመሬት ወረራና ህገወጥ ግንባታ ከመከላከል፣ከቤቶችና ከስራ ዕድል ፈጠራ ጋር በሼዶች ማስተላለፍ ተያይዞ የሚቀርቡ ክርክር ዙርያ እንዲሁም ከዐቃቢ ሕግ ስነ-ምግባር በሚመለከት በልዩ ትኩረት ግምገማው መካሄድ እንዳለበት አሳስበው አስጀምረዋል፡፡በዕለቱ የ2018 በጀት ዓመት የ1ኛ ሩብ አመት ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት የፍትሃብሔር ክርክር ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር በአቶ ናሆም ሰለሞን እንዲሁም የወንጀል ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር በአቶ ሙሴ አንበሴ ቀርቦ ሰፊ ውይይት ተካሄዷል፡፡በዚህም መሰረት በዚህ ሩብ ዓመት የፍትሕብሔር ጉዳዮች ክርክር በፍ/ቤት 3,183 መዝገቦች የነበሩ ሲሆን፣ከዚህ ውስጥ በሩብ ዓመቱ ውስጥ ቀጠሮ በነበራቸው 3,183 መዝገቦች ላይ በፍርድ ቤት እና በማንኛውም የመዳኘት ስልጣን በተሰጠው አካል ተገቢው ክርክር ተደርጓል፡፡ክርክር ከተደረገባቸው 3183 መዝገቦች ውስጥ በ748 የፍትሐብሄር መዝገቦች ላይ ውሳኔ የተሰጠ ሲሆን ከዚህ ውስጥ 686 መዝገቦች ለመንግስት የተወሰነ ሲሆን በ62 መዝገቦች ላይ በመንግስት ላይ ተወስኗል፡፡ ለመንግስት ባስወሰንናቸው መዝገቦች በገንዘብ 1,839,598,183 (አንድ ቢሊየን ስምንት መቶ ሰላሳ ዘጠኝ ሚሊየን አምስት መቶ ዘጠና ስምንት ሺህ አንድ መቶ ሰማኒያ ሶስት) ብር፣ በአይነት ደግሞ 59 ቤቶች፣ 8 ሼዶች እንዲሁም 1,506,881 (አንደ ሚሊየን አምስት መቶ ስድስት ሺህ ስምንት መቶ ሰማኒያ አንድ) ካሬ ሜትር ወይም 150.7 ሄክታር የሚጠጋ መሬት የመንግስት እና ሕዝብ ጥቅም ማስጠበቅ ተችሏል፡፡ በተወሰኑብን 62 መዝገቦች የመርታት92.4% ነው፡፡በመቀጠል የ11ዱም ክ/ከተማ የፍትሐ ብሔር እና የወንጀል ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት የሩብ አመት እቅድ አፈፃፀማቸውን እና ጥያቄዎችን በማቅረብ በዳይሬክተሮቹ ምላሽ ሰጥተዉበታል፡፡የቢሮው ምክትል ኃላፊው አቶ ተስፋዬ ደጀኔ ከቤቱ ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽ በመስጠት የ2018 በጀት ዓመት 1ኛ ሩብ አመት እቅድ አፈፃፀም 92% በላይ በመሆኑ ጥሩ ነው በማለት በወንጀል አያያዛችን በዕርቅ ከመጨረስ አኳያ በተለይ በተፋጠነ ፍትህ ከመስጠት አኳያ በሁሉም ክፍለ ከተማ ጥሩ በመሆኑ አጠናክረን መቀጠል ይኖርብናል ብለዋል ፡፡ኃላፊው አክለውም በመንግስት ፕሮጀክቶች፣ ህገወጥ የመሬት ወረራና ህገወጥ ግንባታ ላይ ፣ የመንግስት ቤቶች ላይ የምመጡትን ክርክሮችን በልዩ ትኩረት ክትትል ማድረግ የሚያስፈልግ እንዲሁም የዐቃቢ ሕግ ከስነ-ምግባር አንጻር በዕውቀት መምራትና ማብቃት ይኖርብናል ሲሉ የመንግስት ቤቶችን ከመፋለም ረገድ በነበሩ ክርክሮች በግል አቤቱታ የቀረቡ ጉዳዮችን በእርቅ ከመጨረስ እና የደንብ ቅጣቶችን ከማስፈፀም አንፃር በልዩ ትኩረት በመስጠት ቅንጅታዊ ስራን ማጠናከር ይገባል ብለዋል፡፡

 


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.