ቢሮው ከባለ ድርሻ አካላት ጋር የ2018 ዓ.ም...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

ቢሮው ከባለ ድርሻ አካላት ጋር የ2018 ዓ.ም 1ኛ ሩብ ዓመት  የቅንጅት ስራዎችን  አፈፃፀም ገመገመ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትህ ቢሮ በ2018 በጀት አመት 1ኛ  ሩብ ዓመት   ቅንጅታዊ ስራዎች አፈፃፀሙን የቢሮው ከፍተኛ አመራሮች ፣ባለድርሻ አካላት፣ የክፍለ ከተማ ፍትህ ጽ/ቤት ሀላፊዎች፣ የቢሮው ዳይሬክተሮች  እና የተለያዩ ሲቪክ ማህበራት  በተገኙበት በጋራ ገምግመዋል ፡፡
በግምገማው  የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት  የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትህ ቢሮ ኃላፊ አቶ ተክሌ በዛብህ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ባስተላለፉበት ወቅት ፍትህ ቢሮ ከተሰጠው ሀላፊነት አንጻር ባለፋት ሶስት ወራት በሕግ ጉዳዮች የአስተዳደሩ ተቋማት አማካሪነቱንና ውክልናውን በተገቢው በመወጣት መብትና ጥቅም ከማስጠበቅ አኳያ መጠነ ሰፊ ስራዎች እንደተሰሩ ገልጸዋል፡፡ 
ኃላፊው አክለውም የታቀዱ ተግባራት ውጤታማ እንዲሆኑ  ከመንግስት ተቋማት እና ከሲቪክ ማህበራት ጋር ስራዎች ያሉበትን ደረጃ መገምገሙ ጥንካሬዎችን በማስቀጠል ሊስተካከሉ በሚገቡ ጉዳዮች ላይ እንዲስተካከሉና እርምጃ በመውሰድ  የቅንጅት ስራው ጉልህ ሚና ነበረው በማለት ቀጣይነት ባለው ሁኔታ ተቀናጅተን የህግ የበላይነቱ እንዲሳለጥ እና እንዲከበር የሁላችንም ሃላፊነት ነው በማለት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡ በሪፖርቱ በዋናነት የቢሮው ዕቅድ አፈጻጸም፣ የቅንጅት ስራዎች አፈጻጸም፣  የተገኙ ውጤቶች እና ውስንነቶች  የፍትህ ቢሮ  የለውጥና መልካም አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ሰቦቃ ገመቹ  ከሰፊ ማብራሪያ ጋር አቅርቧል።የውይይቱ ተሰታፊዎች የ1ኛ ሩብ ዓመት ጠንካራ ስራዎች መሰራታቸውንና ሪፖርቱ ስራዎቹን በሚገልጽ መልኩ ተጠምሮ የተዘጋጀ መሆኑን ጠቅስው ሊስተካከሉ በሚገቡ ጉዳዮች ላይ ሀሳብ አስተያየቶች አንስተዋል፡፡የቢሮው ምክትል ኃላፊ አቶ ተስፋዬ ደጀኔ ስራዎች በመቀናጀት ብቻም ሳይሆን አንድ ሆነው ሲሰራ ውጤታማ መሆን እንደሚቻል እና በቅንጅት ስራዎች ሲሰሩ የተሻለ የፍትህ አሰጣጥ ፣የተሻለ አገልግሎት እና የተሻለ ፍትህ ማስፈን ተጠናክሮ መቀጠል ይገባል ብለዋል፡፡በመጨረሻም የቢሮው ኃላፊ አቶ ተክሌ በዛብህ እና የቢሮው ምክትል ኃላፊ አቶ ተስፋዬ ደጀኔ በተነሱት ሃሳብ አስተያየቶች ምላሽ በመስጠት 1ኛ ሩብ ዓመት ሰፋ ያለ ውጤት የታየበት በመሆኑ በቀሩት ወራት በቅንጅት በመስራትና በማጠናከር የመንግስትና የህዝብ መብትና ጥቅም በማስጠበቅ አፈጻጸማችን ሙሉ ማድረግ ይጠበቅብናል በሚል በአንክሮ ተጠቃልሏል፡፡

04/02/2018


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.