በደንብ ቁጥር 180/2017 ስልጠና መሰጠቱ ዛሬ...

image description
- ውስጥ Laws    0

በደንብ ቁጥር 180/2017 ስልጠና መሰጠቱ ዛሬም እንደቀጠለ ነው፡፡

ስልጠናው በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትህ ቢሮ የሕግ ስርጸትና ምክር መስጠት ዳይሬክቶሬት የተዘጋጀ ሲሆን ከተለያዩ ክ/ከተማ የነዋሪዎች አደረጃጀት ማህበረሰብ ተሳትፈውበታል፡፡
በዕለቱ የስልጠናው መክፈቻ ንግግር ያደረጉት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትህ በህግ ስርፀትና ምክር መስጠት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት ዐቃቢ ሕግ ብርሃን ደመቀ ሲሆኑ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትሕ ቢሮ የህግ ስርፀትና ምክር መስጠት ዳይሬክቶሬት ከሚሰጡት አገልግሎት አንዱ ለከተማ አስተዳደሩ ሰራተኞች እና ለነዋሪዎች በፌደራልም ሆነ በአዲስ አበባ ደረጃ በሚወጡ ህጎች ላይ ግንዛቤ መፍጠር መሆኑን በመግለጽ በዛሬው ዕለትም ከተለያዩ ክ/ከተማ የተወጣጣችሁ የነዋሪዎች አደረጃጀት በደንብ ቁጥር 180/2017 ሰፊ ግንዛቤ እንድትወስዱ ስልጠናው እንደተዘጋጀ በንግግራቸው ገልጸዋል፡፡ስልጠናውን የሰጡት የፍትህ ቢሮ ዐቃቢ ሕግ እስጢፋኖስ አበበ ሲሆኑ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የወንዞች ዳርቻ ልማት እና ብክለት መከላከል ደንብ ቁጥር 180/2017 ስልጠና ሰጥተዋል፡፡
በስልጠናው የደንቡ መዉጣት አስፈላጊነት፣ ወንዞችና የወንዞች ዳርቻን ከብክለት ለመከላከል እንዲቻል የተከለከሉ ተግባራት፣ ደንቡ ከማስፈጸም አኳያ የተቋማት ሃላፊነት እንዲሁም የደንቡን መተላለፍ ስለሚያስከትለዉ ዉጤት በሰፊው ገለጻ አድርገዋል፡፡ዐቃቢ ሕጉ አክለውም ሰዎች ንጹህና ጤናማ አካባቢ የመኖር መብት ከሰብዓዊ መብቶች በሶስተኛነት ደረጃ የሚመደብ በመሆኑ እና በሕገ-መንግስታችን እዉቅና/ጥበቃ ያገኘ መብት በመሆኑ ስልጠናው ያስፈለገበት ምክንያት በመግለጽ ከመኖሪያ ቤት፣ ከአገልግሎት ሰጪ ተቋማት እና አምራች ድርጅቶች የሚወጡ ተረፈ ምርቶች፣ የግንባታና የህንጻ ፍርስራሾች፣ ደረቅ ቆሻሻ እና ሌሎች ተመሳሳይነት ያላቸው በካዮች ወደ ወንዝና በወንዝ ዳርቻ መድፋት ወይም መጣል፣ ማንኛውንም ሰው ፈቃድ ሳይሰጠው የታከመ ፍሳሽን ወደ ወንዝ መልቀቅ፤ በወንዝና በወንዝ ዳርቻ ክልል ውስጥ መጸዳዳት እና ሌሎች በደንብ ቁጥር 180/2017 በአን 7 (1)-(14) በተዘረዘሩት የተከለከሉ ተግባራት ማብራሪያ በመስጠት ደንቡ ከማስፈጸም አኳያ የተቋማት ሃላፊነት እንዲሁም የደንቡን መተላለፍ ስለሚያስከትለዉ ዉጤት ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡በመጨረሻም ከተሳታፊዎች በተነሳው ጥያቄዎች ዐቃቢ ሕጉ ምላሽ በመስጠት ተጠናቋል፡፡


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.