ዳይሬክቶሬቱ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጠ፡፡

image description
- ውስጥ Laws    0

ዳይሬክቶሬቱ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጠ፡፡

ስልጠናው በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትህ ቢሮ የሕግ ስርጸትና ምክር መስጠት ዳይሬክቶሬት የተዘጋጀ ሲሆን የማዕከልና የክ/ከተማ የስርጸት ዐቃቢ ሕጎች እንዲሁም በየተቋማት ላሉ የህግ ባለሙያዎች በስልጠናው ተሳትፈውበታል፡፡በዕለቱም የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የቢሮው ምክትል ኃላፊና የሕግ ጥናት ምርምርና ረቂቅ ዝግጅት እና  የሕግ ስርጸትና ምክር መስጠት ዘርፍ ኃላፊ የሆኑት አቶ አሰፋ መብራቴ በረቂቅ መመሪያ ዝግጅት ወቅት የሚከሰቱ መሰረታዊ ስህተቶች እንዲቀንስ በማድረግ እና ስለ መመሪያ ረቂቅ ዝግጅት በቂ እውቀት እንዲኖራቸው በማድረግ የዕለቱ ስልጠና እንደተዘጋጀ ገልጸዋል፡፡ 

ኃላፊው አክለውም ጥራት ያለው ውጤታማ ሕግ ማስገኘት እንዲቻል የህግ ረቂቅ ዝግጅት በቂ ትኩረት ተሰጥቶት የሚሰራ የህግ አርቃቂ ተግባር እንደሆነ በመግለጽ ቅድመ ረቂቅ፣ በረቂቅ ዝግጅትና ድህረ ረቂቅ ዝግጅት የሚከናወኑ ተግባራት ሂደታቸውን ጠብቀው መከናወን እንደሚኖርባቸው አንስተዋል፡፡

በዕለቱ ስልጠናውን የሰጡት በቢሮው  የሕግ ጥናት ምርምርና ረቂቅ ዝግጅት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ዐቃቢ ሕግ አቶ ጀማል ሣላህ በሕግ ማርቀቅ የመመሪያ ዝግጅት ፣ስለ ሕግ ማርቀቅና የመመሪያ ምንነት ፣የመመሪያ የማውጣት ሂደት፣ ስለሕግ ጥራት መለኪያዎች ፣ የሕግ ንድፍ ማዘጋጀት እንዲሁም በረቂቅ ዝግጅት እና ረቂቅ አርትኦት ዙርያ ሰፊ ግንዛቤ ሰጥተዋል፡፡በመጨረሻም ከተሳታፊዎች በተነሳው ጥያቄዎች የህግ ጥናት ምርምርና ረቂቅ ዝግጅት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ዐቃቢ ሕግ አቶ ጀማል ሣላህ ምላሽ በመስጠት ተጠናቋል፡፡

ጥቅምት 05/2018

ፍትህ ቢሮ

 


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.