የሕግ ረቂቅ ዝግጅትና ም/መስጠት ዘርፍ የጥቅምት ወር እቅድ አፈፃፀም ገመገመ፡፡
በግምገማው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትሕ ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ አሰፋ መብራቴ ፣ የቢሮው የሕግ ስርጸትና ምክር መስጠት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር እንዲሁም የ11ዱም ክ/ከተማ የሕግ ስርጸትና ምክር መስጠት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተሮች ተገኝተዋል፡፡ኃላፊው አቶ አሰፋ መብራቴ በመክፈቻ ንግግራቸው የጥቅምት ወር አፈጻጸሞቻችን ምን እንደሚመስል እና ያጋጠሙ ችግሮች በተለይ በአበይት ተግባራት እና የፍትህ ትራንስፎርሜሽን እቅድ አፈጻጸም ያሉበት ደረጃ ምን እንደሚመስል የምንወያይበት ዕለት ነው በማለት መድረኩን አስጀምረዋል፡፡የ2018 ዓ.ም በጀት ዓመት የጥቅምት ወር ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ያቀሩቡት ዐቃቢ ሕግ ብዙአለም ወንድምሲሻ ሲሆኑ የከተማ አስተዳደሩ ነዋሪና አስፈፃሚ አካላት ንቃተ ሕግ ከማሳደግ አኳያ፣ የሕግ ምክር አገልግሎት ከማሳደግ አኳያ፣ ከትራንስፎርሜሽን እቅድ ጋር በተያያዘ የተሰሩ ስራዎች የያዘ ሪፖርት አቅርበዋል፡፡በዕለቱ የክ/ከ ዳይሬክቶሬቶቹ የጥቅምት ወር እቅድ አፈፃፀም ሪፖርት በጥሩ ሁኔታ እንደቀረበ በመግለጽ በስራ ሂደት ያሉ ተግዳሮቶችን በጥያቄዎቻቸው አንስተዋል፡፡በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትህ ቢሮ የሕግ ስርጸትና ምክር መስጠት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት ዐቃቢ ሕግ ወ/ሪት ብርሃን ደመቀ ከቤቱ በተነሱት ጥያቄዎች ምላሽ በመስጠት ከንቃተ ሕግ ጋር ፣ ከበጀት አጠቃቀም፣ ከሶሻል ሚዲያ አጠቃቀም፣ አንጻር እንዲሁም አስተዳደራዊ ውሳኔን በተመለከተ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡ ዳይሬክቶሬቷ አክለውም የጥቅምት ወር አፈጻጸሙ በአብዛኛው ጥሩ እንደተሰራ በመግለጽ ይህ የሆነው በክረምት በጎ ፍቃድ ስራዎቻችን እንዲሁም በርካታ ስራዎቻችን በቅንጅት በመስራት ነው በማለት ይህን አጠናክረን መቀጠል ይገባል ሲሉ ገልጸዋል ፡፡
ህዳር 09/2018
ፍትህ ቢሮ
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.