በአዋጅ ቁጥር 87/2017 ዓ.ም ስልጠና ተሰጠ፡፡
ስልጠናው በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትህ ቢሮ የሕግ ስርጸትና ምክር መስጠት ዳይሬክቶሬት የተዘጋጀ ሲሆን ለመምህራን ማህበር ሰራተኞች እና ከተለያዩ የትምህርት ተቋማት ያሉ የአስተዳደር ሰራተኞች ተሳትፈውበታል፡፡የስልጠናውን የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሕግ ስርጸትና ምክር መስጠት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ዐቃቢ ሕግ ብርሃን ደመቀ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት በማስተላለፍ በስልጠናው ሰራተኛው መብትና ግዴታውን የሚያውቅበት በደንብና በመመርያ የሚሰራበት ስለሆነ ሰልጣኞች ስልጠናውን በትኩረት እንዲከታተል አስገንዝበዋል፡፡በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ሰራተኛ አዋጅ ቁጥር 87/2017 ዓ.ም የሚያካትታቸውን አጠቃላይ ይዘቶች የመንግስት መስሪያ ቤት መዋቅራዊ አደረጃጀት ፣ የደመወዝ አከፋፈል ፣ ጥቅማ ጥቅም ፣ የደመወዝ ጭማሪ እና ማበረታቻ ስርዓት በቋሚ ሰራተኛነት ለመቀጠር የሚያስችሉ ሁኔታዎች ፣ የመንግስት መረጃ አያያዝና አደረጃጀት ስለቅጥር አፈፃፀም፣ ደረጃ እድገት ፣ስለ ዝውውር እና ፈቃድ ፣የመንግስት ሰራተኞች መብት እና ግዴታ እንዲሁም የአስተዳደር የዲሲፕሊን አወሳሰድ ስለ ቅሬታ ምንነት አቀራረብና አወቃቀር ፣ስለ ቀላልና ከባድ የዲስፕሊን ቅጣት፣እርምጃ አወሳሰድ በሚሉት ርዕሰ ጉዳዮች ዙርያ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትህ ቢሮ ዐቃቢ ህግ አቶ በቃሉ ከበደ ከሰፊ ማብራርያ ጋር አቅርበዋል፡፡
ህዳር 09/ 2018
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.