ወጥ የሆነ የደንብ አፈጻጸም ስርዓት መኖር እንደ...

image description
- ውስጥ Laws    0

ወጥ የሆነ የደንብ አፈጻጸም ስርዓት መኖር እንደሚገባ ተገለጸ፡፡

ይህ የተገለጸው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትህ ቢሮ ከማህበራዊ ፍርድ ቤት ጋር በጋራ በመተባበር ስለ አስተዳደራዊ ቅጣቶችና ደንብ መተላለፍ ፣ የዳኝነት ስልጣን ክስ የመስማት መብት ዙርያ  በተዘጋጀ ስልጠና ላይ ነው፡፡በስልጠናው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትህ ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ተስፋዬ ደጀኔ፣ የማህበራዊ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት አቶ ገ/እግዚአብሔር ፣ የፍትህ ቢሮ ዐቃቢያነ  ሕጎች ፣ የማህበራዊ ፍርድ ቤት ሰብሳቢ ዳኞች እንዲሁም የደንብ ማስከበር ባለስልጣን መካከለኛ አመራሮች ተሳትፈዋል፡፡የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትህ ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ተስፋዬ ደጀኔ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት በማስተላለፍ ከተማችን አዲስ አበባ መጠነ ሰፊ ለውጥ ላይ እንደምትገኝ በመግለጽ ከጽዳት አጠባበቅና ከቆሻሻ አወጋገድ አንጻር  ዜጎች ስለንጽህና ያላቸው ግንዛቤ ምን እንደሚመስል እንዲሁም ከስርዓት ማስከበር አንጻር በከተማ አስተዳደሩ በሚወጡ ደንቦች ዙርያ እንዴት እየተተገበሩ መሆኑን ስልጠናው እንደተዘጋጀ ገልጸዋል፡፡ኃላፊው አክለውም አቃቢያነ ህግ ፣ ዳኞች እና የደንብ ማስከበር ባለስልጣን በመርህ ላይ የተመሰረተ ቅንጅታዊ አሰራርን በመከተል የተቀራረበ መረዳት በመያዝ አንዱ ከአንዱ ልምድ የሚለዋወጥበት እና በደንብ ውሳኔ አፈጻጸም ጋር ተያይዞ በስራ ላይ ያሉ የሚያጋጥሙ ችግሮችን ለመፍታት የሚያስችል ተሳትፎ  የጋራ ግንዛቤ በመኖር ወጥ የሆነ የደንብ አፈጻጸም ስርዓት መኖር እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡በዕለቱ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትህ ቢሮ የህግ ጥናት ምርምር እና ማርቀቅ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ጀማል ሳላህ አስተዳደራዊ ቅጣቶች እና ደንብ መተላለፍ የፍርድ ቤት የዳኝነት ስልጣንና የክስ ሂደትን በተመለከተ የክስ ሂደቱ በምን መንገድ እንደሚመራ በደንብ ቁጥር 167  አስመልክተው ሰፊ ማብራሪያ ሰጥተዋል።በመጨረሻም ተሳታፊዎቹ ስልጠናውን መሰረት በማድረግ ለተነሱት ጥያቄዎች ዳይሬክተር አቶ ጀማል ሳላህ ምላሽ በመስጠት ስልጠናው ተጠናቋል።

ህዳር 10/2018

ፍትህ ቢሮ

 


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.