ለአካል ጉዳተኞች ስልጠና ተሰጠ፡፡
በአ.አ ከተማ አስተዳደር ፍትሕ ቢሮ የህግ ስርፀትና ምክር መስጠት ዳይሬክቶሬት በከተማ አስተዳደሩ ለሚገኙ አካል ጉዳተኞች በስራ ስምሪት አዋጅ ቁጥር 568/2000 ላይ ስልጠና ተሰጠ።ስልጠናውን የሰጡት ዐቃቢ ሕግ አቶ መሰረት ፀሐይ ሲሆኑ አዋጁ በህገ መንግስቱ መሰረት ተጠያቂነት ማስፈን እና የዜጎችን መብት የሚያከብር ህግ እንደሆነ በመግለጽ በአካል ጉዳተኞች የስራ ስምሪት አዋጅ፣ የአካል ጉዳተኞችን የሚመለከቱ ህጎችና እሳቤዎች፣ዕይታዎች እንዲሁምሰብዓዊ መብቶች ስምምነት በሚሉ ርዕሰ ጉዳዮች ዙርያ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡ዐቃቢ ህጉ የአካል ጉዳተኞች ሰብአዊ መብቶች ስምምነት መሰረታዊ ዓላማ የአካል ጉዳተኞችን ሁለመናዊ የሰብዓዊ መብት ክብር የኑሮ ሁኔታ የሚያሳድግ መሆኑን በመግለጽ በአዋጅ 568/2000 የተሰጣቸውን መብቶች እንዲከበርላቸው በፈፃሚው አካል ጥያቄ ማቅረብ እንዲችሉ በተለይ መመሪያን ከማውጣት ከማስፈፀም አንፃር ለዜጋ የተሰጠውን መብት አካል ጉዳተኛውም መብት በመሆኑ ጥያቄያቸውን በማቅረብ ማስፈፀም እንዲችሉ ለማስቻልና በየትኛውም አስፈፃሚ አካላት ለሚያቀርቡት ጥያቄ በጽሁፍ ምላሽ እንዲሰጣቸው መጠየቅ እንዲችሉ ማድረግ እና በተለይም ደግሞ በአስተዳደራዊ ተቋማት ለሚያቀርቧቸው ጥያቄዎች ለሚሰጣቸው ውሳኔዎች ካልረኩ እስከ ፍርድ ቤት በማቅረብ ውሳኔ ሊያሰጡበት እንደሚችሉ በስልጠናቸው ገለጻ አድርገዋል፡፡በመጨረሻም ከቤቱ ለተነሱት ሃሳብ አስተያየቶች ዐቃቢ ሕጉ ምላሽ በመስጠት ስልጠናው ተጠናቋል፡፡
ህዳር15/2018
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.