በአገልግሎት ስታንዳርዳይዜሽን ትግበራ ማስፈጸሚያ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

በአገልግሎት ስታንዳርዳይዜሽን ትግበራ ማስፈጸሚያ ማንዋል ዙርያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትህ ቢሮ በለውጥና መልካም አስተዳደር ዳይሬክቶሬት አዘጋጅነት በአገልግሎት ስታንዳርዳይዜሽን ትግበራ ማንዋል ማስፈጸሚያ ዙርያ ለማዕከልና ለክ/ከተሞች ዳይሬክተሮች እና ለባለሙያዎች ስልጠናው ተሰጥቷል፡፡በስልጠናው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የቢሮው ሃላፊ ተወካይ የሆኑት አቶ ጀማል ሳላህ ከተማ አስተዳደሩ በአገልግሎት አሰጣጡ የተለያዩ የሪፎርም ማሻሻያ ስራ በትኩረት እየሰራ መሆኑን በመግለጽ በአገልግሎት አሰጣጥ ቅልጥፍናን ለማሳደግ አንዱ የለውጥ ስራ በመሆኑ የአገልግሎት አሰጣጡ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሻሻለ በመምጣቱ አገልግሎት አሰጣጣችን ተገልጋዮቻችንን በሚያረካ መልኩ እንድንሰጥ ስልጠናው እንደተዘጋጀ ገልጸዋል፡፡የዕለቱን ስልጠና የሰጡት ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የፐብሊክና የሰው ሃብት ልማት ቢሮ በመጡ የአውትሶርስ ልማት ድጋፍና ቁጥጥር ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ኢሳያስ ግርማ ስታንዳርዳይዜሽን ምን ምን ማሟላት እንዳለበትና የፌደራል አዲሱ ፖሊሲ አቅጣጫውን በሚመለከት 3 ክፍሎች በያዙት ይዘቶች ዙርያ የስታንዳርዳይዜሽን ምንነትና አይነቶች ፣ የትግበራ ማዕቀፎች ፣ የባለሚና አካላት ተግባርና ሃላፊነት እንዲሁም የንጽጽር ምዝገባ ሂደት በሚሉ ርዕሰ ጉዳዮች ዙርያ ሰፋ ያለ ግንዛቤ ሰጥተዋል፡፡በመጨረሻም ከቤቱ የተለያዩ ጥያቄዎች የተነሱ ሲሆን አሰልጣኝ አቶ ኢሳያስ ግርማ ምላሽ በመስጠት ስልጠናው ተጠናቋል፡፡

ህዳር 16/2018

 


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.