ተግባራት የህዝብን ጥቅም ማዕከል ያደረጉ ሊሆን ይገባል ተባለ፡፡
ይህ የተባለው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትህ ቢሮ የ5 ወር መደበኛ ዕቅድ አፈጻጸምና የፍትህ ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ አፈጻጸም በገመገመበት ወቅት ነው፡፡በወቅቱ የቢሮው ከፍተኛ አመራሮች፣ የሁሉም ክ/ከተማ ፍትህ ጽ/ቤት ኃላፊዎችና ዳይሬክተሮች በተገኙበት ግምገማው ተካሄዷል፡፡ግምገማው የወንጀል ሕግ ተፈጻሚነት፣ የአስተዳደር ውሳኔና ሕጋዊነት፣ የፍትሐብሔር ክርክር ውጤታማነት፣ የተጠናከረ ንቃተ -ሕግ ከመፍጠር ዘመናዊ አማራጭ የሙግት መፍቻ ሥርዓቶችን ከማስፋፋት አንጻር ፣ተገቢና ውጤታማ የኅብረተሰብ ተሳትፎ ማረጋገጥ፣ ምቹና ሳቢ የስራ አካባቢ ከመፍጠር አንጻር እንዲሁም ያደገ እና ውጤታማ የኢንፎርሜሽን ኮሚውኒኬሽን ቴክኖሎጂ አጠቃቀም አስመልክቶ ግምገማው ተካሄዷል፡፡የፍትህ ቢሮ ኃላፊ አቶ ተክሌ በዛብህ የግምገማውን መርሃ ግብር ባስጀመሩበት ወቅት ማንኛውም አቅደን የምንተገብራቸው ተግባራት የህዝብን ጥቅም ማዕከል ያደረገ ሊሆን በማለት ለዚህም ደግሞ ዓቃብያነ ሕግ በስነ-ምግባርና በዕውቀት ስራን መምራት እንደሚጠበቅና ዘመኑን የዋጀ አፈጻጸም ሊኖር እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡በዕለቱም የተመረጡት ክ/ከተማ ፍትህ ጽ/ቤት ኃላፊዎች የ5 ወራት ዕቅድ አፈጻጸማቸውን እና የፍትህ ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ አፈጻጸማቸውን የያዘ ሪፖርት አቅርበዋል፡፡ በመጨረሻም የፍትህ ቢሮ ከፍተኛ አመራሮች በቀረበው ሪፖርት እና ከቤቱ በተነሱት ሀሳቦች መነሻ በማድረግ በታዩ ደካማና ጠንካራ ጎኖች አስተያየት በመስጠት የቀጣይ አቅጣጫ በማስቀመጥ ተጠናቋል፡፡
ታህሳስ 07/2018
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.