የፍትሕ ዘርፉን ተደራሽ ለማድረግ ማህበረሰቡን አ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

የፍትሕ ዘርፉን ተደራሽ ለማድረግ ማህበረሰቡን አሳታፊ ያደረገ ስርዓት መዘርጋት ውጤቱ የጎላ እንደሆነ ተገለጸ፡፡

ይህ የተገለጸው የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ፍትህ ሚኒስቴር እና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትህ ቢሮ ባደረጉት የፍትህ ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ አፈጻጸም ውይይት ወቅት ነው፡፡በውይይቱም የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ፍትሕ ሚኒስቴር ሚንስትር ክብርት ወ/ሮ ሀና አርያስላሴ፣ ሚንስትር ደኤታ ኤርሚያስ የማነብርሃን፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትሕ ቢሮ ኃላፊ አቶ ተክሌ በዛብህ እና ሌሎች የዘርፍ አመራሮችና ባለሙያዎች እንዲሁም የማህበረሰብ አቀፍ ፍትሕ መስጫ ማዕከሉ አስታራቂ ሽማግሌዎች እና ተጋባዥ እንግዶች ተሳትፈዋል፡፡በመድረኩም ክብርት ሚኒስትሯ በሀገራችን የፍትሕ ስርዓቱ በመደበኛ የመንግስት ተቋማት ብቻ ታጥሮ መቆየቱ ውጤታማ ባለመሆኑ ማህበረሰብ አቀፍ የፍትህ ስርዓትን በመዘርጋት ማህበረሰቡ ባለው እሴት እና ባህል በእርቅና በመግባባት የየእለት አለመግባባቶችን የመደበኛው ሕግ የሰብአዊ መብት ድንጋገዎች ሳይጣረስ እየተፈታ ይገኛል። በዚህም የፍትሕ ተደራሽነትን ማረጋገጥ፣ በተከራካሪ ወገኖች መካከል ዘላቂ ሰላም መፍጠርና ይወጣ የነበረውን የጊዜና የገንዘብ ብክነትን ማዳን ብሎም የፍርድ ቤቶችን ጫና በመቀነስ የተሳለጠ አገልግሎት መስጠት ማስቻሉን በማውሳት በዚህም ረገድ ፍትሕ ቢሮ እያደረገ ያለው ተግባር አበረታች መሆኑን አድንቀው በቀጣይ ፍትሕ ሚኒስቴር የተጀመሩ ስራዎች እንዲሰፉ እና እንዲቀመሩ ሁሉን አቀፍ እገዛ እንደሚያደርግ ገልጸዋል፡፡የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትህ ቢሮ ኃላፊ አቶ ተክሌ በዛብህ በንግግራቸው ባለፉት ጊዜያት እንደ ሀገርም ሆነ እንደከተማ የፍትህ ዘርፉን ለማሻሻል የተለያዩ የትራንስፎርሜሽን ስራዎች መሰራታቸውንና አገልግሎቶቹ ወደ ሕዝብ ተዳራሽ እየሆነ መምጣቱን አብራርተዋል።የፍትህ ዘርፍ ትራንስፎርሜሸን ፍኖተ ካርታ ተዘጋጅቶ ወደ ተግባር ከተገባበት ከ2016 በጀት ዓመት ወዲህ ዘጠኝ በሚሆኑ ዋና ዋና አማዶች ተግባራት መከናወናቸውንና መስመር እየያዙ መምጣታቸውን በተላይም በማህረሰብ አቀፍ ፍትህ አገልግሎት፣ በሕጎች ተደራሽነት ፣በቴክኖሎጂና በትምህርት ቤት ክበባት ጨምሮ በጎ ፍቃደኞች በማሳተፍ እቅዶችን ማሳካት መቻሉን አስረድተዋል። በተያያዘም ክብርት ሚንስትሯ በቢሮ ኃላፊ የቀረቡ የትራንስፎርሜሽን ተግባራት ሞደል ሆኖ እንዲያድግ በተመረጡ ዘርፎች ተቀናጅተው እንደሚሰሩም አረጋግጠዋል።ክብርት ሚንስትሯ ከፍትሕ ቢሮ ጉብኝትና ስራ ግምገማ በተጨማሪ በሀገርቱ ብቸኛ የሆነውን በከተማ አስተዳሩ ሴቶች ሕጻናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ የሚተዳደረውን ወጣት ጥፋተኞች ተሃድሶ ማዕከል ጉብኝት ያደረጉ ሲሆን የቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ቆንጂት ደበላ እና የተቋቋሙ ስራ አስፈጻሚ አቶ እንግዳ መንግስቱ በተቋሚ የሚሰጡ አገልግሎቶችንና የሚስተዋሉ ማነቆዎችን አስመልክቶ ሰፋ ያለ ገለጻ ቀርቦ ቀጣይ በጋራ በሚሰሩባቸው ጉዳዮች ውይይት ተደርገውበታል።

ታህሳስ 09/2018

 


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.