ቢሮው በ2018ዓ.ም በግማሽ አመት ውስጥ ሶስት...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

ቢሮው በ2018ዓ.ም በግማሽ አመት ውስጥ ሶስት ቢሊየን 212 ሚሊየን 856 ሺ,060.18 ብር የሚገመት የመንግስትና የህዝብ መብትና ጥቅም ማስጠበቅ ችሏል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትህ ቢሮ የ2018 በጀት ዓመት የ6 ወር የዕቅድ አፈጻጸም፣ በመልካም አስተዳደር ችግሮች፣ ቅሬታ አፈታት እና በሌብነትና ብልሹ አሰራር ዕቅድ አፈጻጸም ከቢሮው አመራሮች፣ከ11ዱም ክ/ከተማ የፍትህ ጽ/ቤት ኃላፊዎች፣ ከሰራተኞች እንዲሁም ከባለድርሻ እና ሲቪክ ማህበራት ጋር ውይይት አካሄደ፡፡

በውይይቱ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትህ ቢሮ ኃላፊ አቶ ተክሌ በዛብህ የመክፈቻ ንግግር ባደረጉበት ወቅት ቢሮው በአስፈጻሚ አካላት በወጣው አዋጅ ቁጥር 84/2016 ለከተማውና ለነዋሪው መብትና ጥቅም በማስጠበቅ በጸደቁ ህጎች ላይ ለነዋሪው ከማድረስ አኳያ ከፍተኛ ስራ እየሰራ እንደሚገኝ በመግለጽ በግማሽ ዓመት ውስጥ በህግ ጉዳዮች ክርክር አፈጻጸም ሶስት ቢሊየን 212 ሚሊየን 856 ሺ,060.18 ብር ፣ በአይነት 101 ቤቶች፣ 19 መስሪያ ቦታ ሼዶች፣ 178.62 ሄክታር መሬት ማስከበር መቻሉን የመንግስትና የህዝብ መብትና ጥቅም ማስጠበቅ መቻሉን ገልጸዋል፡፡

ኃላፊው አክለውም በወንጀል ሕግ አፈጻጸም ከቀረቡ የግል አቤቱታ የወንጀል ምርመራ መዝገቦች 85.6% በዕርቅና በመግባባት እንደተጨረሰ በማንሳት ከሰነድ በማዘጋጀትና የስልጠና መድረክ በማዘጋጀት ህጎችን ለነዋሪው ከማስረጽ ረገድ ከፍተኛ ስራ እንደተሰራና ጥሩ ውጤት አፈጻጸም መምጣቱን በመግለጽ ይህ ውጤት እንዲመጣ ላደረጉት በየደረጃው ያሉ አመራሮች ፣ ዐቃቢያነ ሕጎች፣ የክ/ከተማ ፍትህ ጽ/ቤት ኃላፊዎች፣ በየዘርፉ ላሉ ሰራተኞች በአጠቃላይ ለሁሉም ባለድርሻ አካላት ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡

የ2018 በጀት ዓመት የ6 ወር ሪፖርት ያቀረቡት በቢሮው የዕቅድና በጀት ዝግጅት ክትትልና ግምገማ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ደሳለኝ በላይ ሲሆኑ በህግ ጉዳዮች ክርክር አፈጻጸም ውጤታማነት ከማሳደግ አኳያ፣ከወንጀል ሕግ አፈፃፀም ውጤታማነትን፣ ከንቃተ ሕግ፣ ከህግና ፍትህ ማሻሻያ ስራዎችን ውጤታማነት፣ ከአቃቢያን ሕግ ውሳኔ ኦዲት እና ኢንስፔክሽን ምርመራ ፣ከሰብዓዊ መብት አከባባርና ከህገወጥ የሰዎች ዝውውርን ከመከላከል ብሎም በቁልፍ ሥራዎች አፈፃፀም፣ በተጠሪ ተቋም የአበይት ተግባራት ዕቅድ አፈፃፀም እና በተገኙ ውጤቶች እና በነበሩ ጥንካሬዎች ዙሪያ በዝርዝር አብራርተዋል፡፡

በመጨረሻም ከቤቱ ለተነሱት ጥያቄዎችና አስተያየቶች በቢሮው ኃላፊ አቶ ተክሌ በዛብህ እና ምክትል ኃላፊ አቶ አሰፋ መብራቴ ምላሽ ተሰጥቶበት በቀጣይ ቀሪ ወራቶች መሰራት በሚገባቸው ዙርያ በተለይ በስነምግባር የታነጸ አገልጋይ ባለሙያ ከማጠናከር፣ የፍትህ ዘርፍ ትራንስፎርሜሽን ፣ የቴክኖሎጂ ልማትና አጠቃቀም ዙሪያ ትኩረት እንደሚሰጥባቸው አቅጣጫ ተሰጥቶበት ተጠናቋል ፡፡

ጥር05/2018

 


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.