ቢሮው  ዜጎች በፍትሕ ስርዓት ላይ እምነት እንዲ...

image description
- ውስጥ Laws    0

ቢሮው  ዜጎች በፍትሕ ስርዓት ላይ እምነት እንዲኖራቸው ፣ የሕግ የበላይነት እንዲከበር እና ሀገር ወዳድ ትውልድ ለማፍራት እየሰራ ይገኛል

ቢሮው  ዜጎች በፍትሕ ስርዓት ላይ እምነት እንዲኖራቸው ፣ የሕግ የበላይነት እንዲከበር እና ሀገር ወዳድ ትውልድ ለማፍራት እየሰራ ይገኛል ።ለዚህም ከመደበኛ የፍትሕ ስርዓት በተጨማሪ በነባር ባሕሎቻችን ችግሮችን ለመፍታት የሚያስችል የማሕበረሰብ አቀፍ የፍትህ አገልግሎት እንዲተገበር በርካታ ስራዎች እየተሰራ ይገኛል። የማህበረሰብ አቀፍ ፍትህ አገልግሎት ማህበረሰቡ ባለው ነባር እሴት የወንድማማችነት እና የእህትማማችነት ኢትዮጵያዊ መተሳሰብና መቻቻል ግጭቶች ሲፈጠሩ የምንፈታበት የዳበረ  ባህላችንን ማረጋገጫም ጭምር ነው።ማህበረሰቡ በወንጀልም ሆነ በፍታብሔር ክርክር ጊዜያቸውን፣ ገንዘባቸውንና ጉልበታቸውን እንዳያባክኑ የሚያግዝ መሆኑ ታምኖበት በመንግስትም ተቋማት የመደገፉና የማስፋቱ ስራ በዕቅድ ተይዞ በመሰራቱ በዚህም ብዙ መሻሻሎችን በፍትህ ስርዓት አምጥቷል።ይሕንን አሰራር ተደራሽ ለማድረግ እና በስነምግባር የታነፀ እና ንቁ ትውልድ ብሎም በምክንያት የሚያምን በምክንያት ደግሞ የሚሞግት ትውልድ ለመፍጠር  በትምህርት ቤቶች የንቃተ ሕግ ክበባት በማቋቋም ንቃተ ሕግ እየተፈጠረ ይገኛል።ዛሬ የዚሁ አካል የሆነው በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ተማ ፍትሕ ጽ/ ቤት ለተከታታይ ሲካሄድ የነበረው የምስለ ችሎትና ሙግት ውድድር መርሃ ግብር ዛሬ የከተማ አስተዳደሩ ፍትህ ቢሮ ፣ ትምሕርት ቢሮ እንዲሁም በክፍለከተማው የሚገኙ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች በተገኙበት ተካሂዷል።


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.