በመኖሪያ ቤት ኪራይ ቁጥጥር እና አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 1320/2016 እና አዋጁን ተከትሎ በወጡ መመሪያዎች አፈጻጸም ላይ ያተኮረ ዉይይት ተደረገ፡፡
በመኖሪያ ቤት ኪራይ ቁጥጥር እና አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 1320/2016 እና አዋጁን ተከትሎ በወጡ መመሪያዎች አፈጻጸም ላይ ያተኮረ ዉይይት ተደረገ፡፡
በዉይይት መድረኩ የፍትህ፣ የይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት፣ የሠላምና ጸጥታ፣ የቤቶች ልማትና አስተዳደር፣ የመልካም አስተዳደርና አቤቱታ ዘርፍ፣ የሴቶችና ማሕበራዊ ጉዳይ ቢሮና በተዋረድ ያሉ የጽህፈት ቤቶቻቸው ስራ ኃላፊዎች እንዲሁም ሌሎች ባለድርሻ በተገኙበት በመኖሪያ ቤት ኪራይ ቁጥጥር እና አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 1320/2016፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ የወጣ የመኖሪያ ቤት ኪራይ ቁጥጥር እና አስተዳደር መመሪያ እንዲሁም በከተማ አስተዳደሩ ካቢኔ የጸደቀ የመኖሪያ ቤት ኪራይ ጉዳዮች አቤቱታ ሰሚ ኮሚቴ የአደረጃጀት እና የአሰራር መመሪያ ቁጥር 164/2017 አፈጻጸም ላይ ያጋጠሙ ክፍተቶችና ቀጣይ አቅጣጫ ላይ በዝርዝር ሁለት ሰነድ ቀርቦ ውይይት ተደርጓል፡፡
በውይይቱም የሕግ ማቀፎቹ የዜጎች የንብረት የማፍራትን መብት በእጅጉ ያከበሩ ተያይዞም ምክንያታዊ ባልሆነ አኳኃን በየጊዜው ነዋሪዎች ላይ ጫና የሚያሳድረው የመኖሪያ ቤት ክራይ ዋጋ ቁጥጥር መደረጉ አስተዳደሩ በሺዎቹ በየግዜው በተለያዩ ሞዳሊቲዎች ለነዋሪዎች እያለማ የሚያቀርባቸው የቤት አማራጮችን ከመደገፍ ረገድና የኑሮ ጫና ከማረጋጋት አኳያ ከፍተኛ አበርክቶ እንዳለውም ተብራርቷል፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ በአፈጻጸም ወቅት ያጋጠሙ ውስንነቶችን በአከራይ ተከራይ፣ ተቆጣጣሪ አካል እና የመኖሪያ ቤት ኪራይ ጉዳዮች አቤቱታ ሰሚ ኮሚቴ በመናበብ በዘርፉ ነዋሪዎች የሚፈልጉት አገልግሎት ማቀላጠፍ እንዳለበት በውይይት ወቅት ተነስተው ለቀጣይ ግዜያት ባለድርሻ አካላት ድርሻ ድርሻቸውን በመከፋፈል መድረኩ ማብቂያ አግኝቷል፡፡
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.