አዲሱ የፍትህ ቢሮ ኃላፊ የሥራ ርክክብ አደረጉ።

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

አዲሱ የፍትህ ቢሮ ኃላፊ የሥራ ርክክብ አደረጉ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት በክብርት ከንቲባ አዳነች አቤቤ አቅራቢነት የከተማውን አዲስ የካቢኔ አባላት ሹመት ማጽደቁን ተከትሎ፣ በፍትህ ቢሮ የኃላፊነት የሥራ ርክክብ ሥነ-ሥርዓት ተከናውኗል።

በዚህም መሠረት የቢሮው አዲስ ተሿሚ ኃላፊ አቶ ተስፋዬ ደጀኔ ከቀድሞው የቢሮ ኃላፊ አቶ ተክሌ በዛብህ ጋር በይፋ የሥራ ርክክብ አድርገዋል።

በሥራ ርክክብ መድረኩ ላይ እንደተገለጸው፣ የከተማ አስተዳደሩ የሕግ የበላይነትን ለማረጋገጥ፣ የነዋሪዎችን ፍትህ ተደራሽነት ለማሻሻል እና የተጀመሩ የፍትህ ሥርዓት ማሻሻያ ሥራዎችን ይበልጥ አጠናክሮ ለማስቀጠል አዲሱ አመራር በትኩረት እንደሚሠራ ተገልጿል።

የቀድሞው ኃላፊ አቶ ተክሌ በዛብህ በነበራቸው የኃላፊነት ቆይታ ተቋሙን በምክትልነት አብረው ሲመሩ ለነበሩትና አሁን ኃላፊነቱን ለተረከቡት አቶ ተስፋዬ ደጀኔ መልካም የሥራ ዘመን የተመኙ ሲሆን፣ አዲሱ ኃላፊም ለተደረገላቸው አቀባበልና እምነት ምስጋና አቅርበው ተቋማዊ ተልዕኮውን ለማሳካት በቁርጠኝነት እንደሚሰሩ ገልጸዋል።

 


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.