ቢሮው  የ2019 በጀት ዓመት 1ኛ ሩብ ዓመት ዕ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

ቢሮው  የ2019 በጀት ዓመት 1ኛ ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም  ግምገማ አካሄደ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትሕ ቢሮ የ2019 ዓ.ም. የመጀመሪያ ሩብ ዓመት አፈጻጸሙን በመገምገም የቀጣይ የሥራ አቅጣጫዎችን አስቀምጧል።በግምገማው በፍትሕ ቢሮ በኩል የተሰሩት የመንግሥትና የሕዝብን ጥቅም  ማስጠበቅ ፤ የሕግ ግንዛቤን ማስፋፋት፣ የሕግ ምክርና አገልግሎትን ማጠናከር፣ እንዲሁም የፍትሕ ሥርዓቱን ውጤታማና ተደራሽ ለማድረግ የሚደረጉ ተግባራት ተገምግመዋል።የቢሮው ኃላፊ አቶ ተስፋዬ ደጀኔ በግምገማው መድረክ ባደረጉት ንግግር፣ የተቋሙ አፈጻጸም የሚመዘነው ምን ያህል ተግባር ተከናወነ በሚለው ብቻ ሳይሆን፣ የተከናወነው ሥራ የከተማ አስተዳደሩ የጀመራቸዉን ሁለንተናዊ  የልማትና የመልካም አስተዳደር ሪፎርም  ተግባራዊ  እንዲሆን  እንዲሁም በሕዝብ  ዘንድ ምን ዓይነት ተጨባጭ ለውጥ አመጣ በሚለው መሆን እንዳለበት አስገንዝበዋል።ኃላፊው አክለውም የፍትሕ ቢሮ ሥራዎች ከሕዝብ ጥቅም ጋር በቀጥታ የተሳሰሩ በመሆናቸው የሥራ አፈጻጸምን በቁጥር ብቻ ሳይሆን በጥራት፣ በውጤትና በዜጎች የፍትሕ አገልግሎት ተሞክሮ መመዘን እንዳለበት ጠቁመዋል።ከተመዘገቡ ውጤቶች በተጨማሪ በአፈጻጸም የታዩ ክፍተቶች ተለይተው ለእያንዳንዱ ችግር ተግባራዊ መፍትሔ እንዲቀመጥ አቅጣጫ ተሰጥቷል።በተለይም የሥራ ዕቅዶች ከተቋሙ ተልዕኮ ጋር ተጣጥመው እንዲፈጸሙ፣ የተጠያቂነት ሥርዓት እንዲጠናከርና የተጀመሩ ሥራዎች በውጤት እንዲጠናቀቁ አፅንዖት ተሰጥቷል።በመድረኩ የተነሱ ሀሳቦችና የተቀመጡ አቅጣጫዎች በቀጣይ የሥራ ወቅት የቢሮውን አፈጻጸም በማሻሻል፣ የፍትሕ አገልግሎትን ማጠናከር እንደሚገባ  ተገልጿል።በመሆኑም በቀጣይ የሥራ ወቅት የተቋሙን የአፈጻጸም አቅም ማጠናከር፣  የሥራ ቅልጥፍናን ማሳደግ፣ ተጠያቂነትን ማጠናከርና የዓቃቢ ህግ ስነ-ምግባር እንዲሁም ከቴክኖሎጂ አጠቃቀም ጋር በተያያዘ በትኩረት እንዲሠራበት አሳስበዋል።የአፈጻጸሙን ሪፖርት ያቀረቡት የዕቅድና በጀት ዝግጅት፣ ክትትልና ግምገማ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ደሳለኝ በላይ ናቸው።

መስከረም28/2019 ዓ.ም.
ፍትህ ቢሮ


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.