የሚዲያ ህግ፤ሀሳብን በነፃነት የመግለጽ መብትና የጋዜጠኞች ደህንነት !
የመረጃ ነፃነት የዜጎችን የመረጃ የማግኘት መብት ከማረጋገጥ ባለፈ፣ ግልጽነትን፣ ተጠያቂነትንና ዴሞክራሲያዊ ሥርዓትን ለማጠናከር ወሳኝ ሚና አለው። የጋዜጠኞችን ደህንነት መጠበቅና ሚዲያዎች ሙያዊ ኃላፊነታቸውን በነፃነት እንዲወጡ ማስቻልም ለዚህ ወሳኝ ነው።
በዚህ መሠረት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትሕ ቢሮ ከኢትዮጲያ ሰብአዊ መብቶች ድርጅት ጋር በመተባበር ለሕግ አካላት በሚዲያ ሕግ፣ በመረጃ ነፃነትና በጋዜጠኞች ደህንነት ጉዳዩ ከማመለከታቸው የህግ አካላት ጋር ውይይት አድርጓል።
መንግሥት የመረጃ ነፃነትን ለማረጋገጥና የመረጃ ተደራሽነትን ለማሻሻል እየሠራ መሆኑን ገልጸው፣ የሚዲያ ነፃነትን ከሕጋዊ ኃላፊነት ጋር በማጣመር የሕግ የበላይነትን ማጠናከር እንደሚገባ የፍትሕ ቢሮ የጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ግርማ ወርቁ በውይይቱ አስገንዝበዋል።
ኃላፊው አክለውም ጋዜጠኞች ሙያዊ ተግባራቸውን በነፃነት እንዲያከናውኑ ሕጉን እንዲገነዘቡ እና በሕግ እንዲመሪ ማስቻል እንደሆነ ጠቁመዋል።
በውይይት የሕግ አካላት በሚዲያ ሕግና በመረጃ ነፃነት ዙሪያ ያላቸውን ግንዛቤ በማሳደግ፣ የጋዜጠኞችን መብት ለማስጠበቅና የሕግ የበላይነትን ለማጠናከር ያለመ ነው።
የመረጃ ነፃነት፣ የጋዜጠኞች ደህንነትና የሕግ የበላይነት ለግልጽና ተጠያቂ አስተዳደር!
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.