ህብረ-ብሔራዊ አንድነታችን የጥንካሬያችን ምሰሶ ነው!
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትህ ቢሮ ለ21ኛ ጊዜ የሚከበረውን የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓል ምክንያት በማድረግ "በብዝሃነት የደመቀች በምክክር የጸናች ኢትዮጵያ" በሚል መሪ ቃል የፍትህ ቢሮ አመራሮች እና ሰራተኞች በተገኙበት የፓናል ውይይት አካሄደ ።
በዕለቱም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትህ ቢሮ ሃላፊ በመክፈቻ ንግግራቸው ሀገራችን ኢትዮጵያ በባህላችን፣ በቋንቋችን እና በማህበራዊ አኗኗራችን ውብ የሆነ ብዝሃነት የተጎናጸፈች ሀገር በመሆኗ ይህንን ውብ ብዝሃነታችንን ተቀብለን፣ በአብሮነትና በመተማመን ላይ የተመሠረተ ጠንካራ የፌደራል ሥርዓት መገንባት ያስፈልጋል በማለት የሀገራችንን ሰላም፣ ዴሞክራሲያዊ አንድነትና ሁለንተናዊ ብልጽግና ከፍ ለማድረግ በጋራ መቆም ይኖርብናል ሲሉ ገልጸዋል።
የቢሮው ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ግርማ ወርቁ "የብዝሃነት አስተዳደር እና የመንግስታት ግንኙነት ለጠንካራ የፌደራል ስርዓት ግንባታ" በሚል መነሻ ርዕስ የፓናል ውይይት ሰነዱን ያቀረቡ ሲሆን የብዝሃነት አስተዳደር እና ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት፣
ሀገራዊ ምክክር እና የውይይት ባህል፣ ተቋማዊ የመንግስታት ግንኙነት፣ የብዝሃነት አስተዳደር ዕድሎችና ፈተናዎች፣ በሚሉ ነጥቦች ትኩረቱን ያደረገ ሰፊ ማብራሪያ አቅርበዋል።
በመጨረሻም የፍትህ ቢሮ ሃላፊ አቶ ተስፋዬ ደጀኔ፣ የታክስ ይግባኝ ኮሚሽን ፕሬዝዳንት አቶ ታረቀኝ አስፋው፣ የፍትህ ቢሮ ምክትል ሃላፊ አቶ ገለታ ቶላ አወያይነት ተጠናቋል።
08/03/2019 ዓ.ም
ፍትህ ቢሮ
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.