ቢሮው የስድስት ወራት እቅድ አፈፃፀም  ገመገመ

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

ቢሮው የስድስት ወራት እቅድ አፈፃፀም  ገመገመ

ጥር 8 ቀን 2016


የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትህ ቢሮ የ2016 በጀት  አመት የስድስት ወራት አፈፃፀም አመራሮችና ሰራተኞች በጋራ ገምግሟል።


በሪፖርቱ በዋናነት የወንጀል ጉዳይ አፈፃፀም፣በተረቀቁ ህጎች ፣ በፍታብሔር ጉዳዩች የከተማ አስተዳደሩንና የናዋሪውን መብት ከማስጠበቅ አንፃር፣ለከተማ አስተዳደሩ ህጎችን ለማሳወቅ በሚሰሩ የስርፀት ስራዎች፣ሰባዊ መብትን ከማስከበርና ፣በሰው መነገድ እና ሰውን በህገወጥ መንገድ ደንበር የማሻገር ወንጀልን በተመለከተ  የነበሩ ጠንካራና ደካማ ጎኖች እና የገጠሙ ችግሮች የመፍትሄ አቅጣጫ በስፋት በቢሮው የእቅድና በጀት ክትትል ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ደሳለኝ በላይ ቀርበዋል፡፡


የፍትህ ቢሮ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ግርማ ወርቁ በመክፈቻ ንግግራቸው  አፈጻጸሞችን ወቅቱን ጠብቀን መገምገማችን ስራዎችን በጥንካሬ እና በድክመት በመለየት መልካም አፈጻጸሞቻችን ገፊ ምክንያታቸውን አውቆ እንደ ተሞክሮ በመውሰድ በድክመት የታዩትን እንዳይደገሙ በመስራት ተቋሙን  ውጤታማ ማድረግ ነው ብለዋል።


በመጨረሻም የፍትሕ ቢሮ ኃላፊ አቶ ተክሌ በዛብህ ከቤቱ በተሳታፊዎች በተነሱት ጉዳዮች መድረኩን ሲያጠቃልሉ በግማሽ ዓመቱ የቢሮው አፈጻጸም የተሻለ እንዲሆን ሁሉም ሰራተኛ የራሱ ድርሻ እንደተወጣ በመግለፅ የነቃ ተሳትፎ ላደረጉ ሰራተኞች ምስጋናቸውን በማቅረብ በቀጣይ ቢሮው ከዚህ የተሻለ አፈጻጸም ኖሮት ተወዳዳሪ ተቋም እንዲሆን ሁሉም ለውጤት መትጋት አለበት ብለዋል።
በወቅቱ ቢሮው  የስድስት ወራት አፈፃፀሙን ወቅቱን ጠብቆ ሁሉም ሰራተኞች ባሉበት መገምገሙ ለቀጣይ ቀሪ ወራቶች የሚያዘጋጅ መሆኑን በመግለጽ የተለያዩ ሀሳብ አስተያየት ጥያቄም ጭምር በማንሳት ውይይት በማድረግ  በቀጣይ መሻሻል ባለባቸው ጉዳዮች ላይም ውይይት መደረጉ ቀጣይነት እንደሚኖረው አረጋግጠዋል


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.