በመጪው የከተራ እና የጥምቀት በዓል አከባበር ዙሪያ ውይይት ተደረገ።
በመጪው የከተራ እና የጥምቀት በዓል አከባበር ዙሪያ ውይይት ተደረገ።
ጥር 06/2016
የውይይት መድረኩን የመሩት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የፍትህ ቢሮ አማካሪ የሆኑት ወ/ሮ ዘርፈሽዋል ንጉሴ የጥምቀት በዓል በዩኒስኮ የተመዘገበ ሀገራችንን ለሌሎች የአለም ያስተዋወቀ ትልቅ በዓላችን ነው ብለው በዓሉ ሀይማኖታዊ ስርዓቱን በጠበቀ መልኩ እና ሰላማዊ ሆኖ ባህልና ትውፊቱን በጠበቀ መንገድ እንዲከበር ሀሉም ሃላፊነቱን እንዲወጣ ጠይቀዋል፡፡
በወቅቱ የፍትህ ቢሮ አማካሪ ወይዘሮ ዘርፈሽዋል ንጉሴ አከባበሩን አስመልክቶ ሰነድ አቅርበው አወያይተዋል።
የውይይቱ ተሳታፊዎች የጥምቀት በዓል የአብሮነት፣የወንድማማችነት/እህትማማችነት እና የፍቅር መገለጫ የሆነ በመሆኑ ሰላማችንን ማስጠበቅ ሀገራዊ ግዴታችን ነው በማለት ቢሮው አስቀድሞ መሰል መረጃዎችን መስጠቱ እጅግ የሚያስመሰግነው ነው ብለዋል፡፡
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.