የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትህ ቢሮ 2016 በጀት አመት አመታዊ እቅድ አፈፃፀም እና የ2017 በጀት ዓመት አመታዊ እቅድ ላይ ውይይት አካሄደ
ሰኔ 24/10/2016 ዓ.ም
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትህ ቢሮ በ2016 በጀት አመት አመታዊ እቅድ አፈፃፀም ላይ እና የ2017 በጀት ዓመት ጠቋሚ አቅድ የቢሮው ከፍተኛ አመራሮች፣የክፍለ ከተማ የፍትህ ጽ/ቤት ኃላፊዎችና ዳይረክተሮች፣ የቢሮው ዳይሬክተሮች እና ባለሙያዎች በተገኙበት ውይይት አካሂደዋል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትህ ቢሮ ኃላፊ አቶ ተክሌ በዛብህ የ2016 በጀት ዓመቶ አፈፃፀም እና የ2017 በጀት ዓመት እቅድ ያቀረቡ ሲሆን በይዘትም በፍተሐብሄር ጉዳዮች የከተማ አስተዳደሩን የነዋሪውን መብትና ጥቅም ከማስጠበቅ አንፃር ፣ ከህግ ኦዲት ኢንስፔክሽን ፣ከሰብአዊ መብት ማከባበር ፣ከሰው መነገድ እና በህገወጥ መንገድ ደንብር ማሻገር ወንጀልን ከመከላከል አንፃር ፣ ከወንጀል ህግ አፈፃፀም አንፃር፣ከንቃተ ሕግ ግንዛቤ ማሰጨበጥ ፣ከህግና ፍትህ ማሻሻያ ስራዎችን ከማሳደግ አንፃር፣ከሰው ሀብት፣ከኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን እና ቴክኖሎጅ አሰራርንና ውጤታማነትን ከማሳደግ አንፃር እና የህዝብ ግንኙነት ስራዎችን ከመስራት አንፃር የተሰሩ ስራዎችን አፈፃፀም እንዲሁም የ2017 በጀት ዓመት መሪ እቅድ በዝርዝር አቅርበዋል፡፡
በወቅቱ የክፍለ ከተማ የፍትህ ጽ/ቤት ኃላፊዎች እና ዐቃቢያነ ህግ በቀረበው ሰነድ መነሻነት ስራዎቻቸውን ያማከለ ሀሳብ፣ጥያቄና አስተያየቶችን አቅርበዋል፡፡
የቢሮው ኃላፊ አቶ ተክሌ በዛብህ በማጠቃለያቸው ከተማ አስተዳደሩ በሁሉም ሴክተር በፍጥነት እና በጥራት 7/24 በመስራት ተጨባጭ ውጤት እያሳየ ይገኛል በማለት ፍትህ ቢሮም በሚያደርጋቸው ክርክሮች በሚያረቃቸው ህጎች፣ በሚያዘጋጀው ውሎች ከቀደመው አሰራር ተላቅቆ በፍጥነትንና ፈጠራን ያማከለ ስራ ውስጥ ካልገባ ከከተማው አሁናዊ የስራ አተገባበር ጋር እኩል መራመድ አይቻልም፣ ይህ ካልሆነ እንቅፋት መሆን ነው በማለት በተለየ ርብርብ እና ቅልጥፍና መስራት የሚያስችል እቅድ በማቀድ መስራት ያስፈልጋል በማለት በቀጣይ በትኩረት ሊሰራ ይገባል ያሉት አቃቢ ህጉን ለማብቃት ማሰልጠን፣የሰውሀይሉ ብቃትና ጥራት ያለው ለማድረግ የአሰራር ስርዓት መዘርጋት የህግ ማእቀፎችን ማዘጋጀት፣ በሚሰጡ ውሳኔዎች ላይ አፈፃፀማቸውን ተከታትሎ ማስፈፀም ፣የወጡ ህጎችን የማስረፅ ስራ መስራት፣የሰብአዊ መብት አጠባበቅን እና በሰው የመነገድ ወንጀልን መከላከል የሚያስችል ስራዎችን አጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡
በመጨረሻም ኃላፊው ከቤቱ ለተነሱት ጉዳዮች ለተነሱት ጥያቄዎች ምላሽ በመስጠት በአፈፃፀሙ ለተካፈሉ ሁሉም የቢሮው አባላት ምስጋና በማቅረብ ለቀጣይ 2017 በጀት አመት በተሻለ የስራ ተነሳሽነት ኖሮን ከተማችንን እንደ ራእያችን ሁሉ ፍትህ የሰፈነባት ከተማ ለማድረግ የድርሻችንን እንወጣ የሚል መልክት አስተላልፈው መድረኩ ተጠናቋል፡፡
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.