በሰው የመነገድ ሰውን በህገወጥ መንገድ ድንበር የማሻገር ወንጀልን መከላከል በሚያስችል አሰራር ዙሪያ ውይይት ተካሄደ።
ቀን 21/10/2016 ዓ. ም
ውይይቱ በሰው የመነገድ ሰውን በህገወጥ መንገድ ደንበር ማሻገር ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ከሕይወት ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር ለአዲስ አበባ ምክርቤት ቋሚ ኮሚቴዎች ፣ ከአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ለመጡ እና አዲስ አበባ ፍትህ ቢሮ አቃቢ ሕጎች የማስተባበሪያ ጽ/ቤት በህግ ማእቀፎች በተዘርጋው አደረጃጀት እና አሰራር ላይ እንዲሁም የወንጀሉን ዓለም አቀፍ ይዘት የሚያሳዩ ሰነዶች ቀርበዋል ።
በአዲስ አበባ ከተማ ፍትህ ቢሮ በሰው መነገድ ሰውን በህገወጥ መንገድ ድንበር ማሻገር ወንጀልን መከላከል ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ታደሰ ፈይሳ በመክፈቻ ንግግራቸው ወንጀሉ ዘርፈ ብዙ እጆች ስለሚሳትፉበት በጋራ በቅንጅት መከላከል እንደሚገባ ጠቅሰው በከተማ አስተዳደሩ ጉዳዩን አስመልክቶ የሚፈጸመውን ወንጀል ለመከላከል የጋራ አቋም እና ግንዛቤ ያስፈልጋል በማለት የማስተባበሪያ ጽ/ቤት በህግ ማእቀፎች በተዘረ ጋው አደረጃጀት እና አሰራር ላይ እንዴት እየተሰራ እንደሆነ የሚያሳይ ሰነድ በማቅረብ ገለፃ አድርገዋል።
በሰው መነገድ ሰውን በህገ ወጥ መንገድ ድንበር ማሻገር ወንጀል መከላከል ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ዓቃቤሕግ አቶ ነብዩ በቀለ የህገወጥ የሠዎች ዝውውር ወንጀል አለም ዓቀፋዊ ባህሪ እንዳለዉ እና በአህጉር አቀፍ እና በሀገር አቀፍ ደረጃ ምን ላይ እንዳለ የወንጀሉ ዋና ምክንያቶች እና አላማ የሚያሳይ ሰነድ ሰፊ ማብራሪያ በመስጠት ስልጠና ሰጥተዋል ::
የአዲስ አበባ ፖሊስ የልዩልዩ ወንጀሎች ምርመራ ማሰተባበሪያ ኃላፊ ኢ/ር ቶልቻ ዳዲ ወንጀሉ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከክፍለ ከተማ ክፍለ ከተማ ያለውን የወንጀል ፍሰት እና የተወሰዱ እርምጃዎች አስመልክቶ ማብራሪያ ሰጥተዋል።
በሰው የመነገድ ወንጀል ትልቅ አጀንዳ እንድመሆኑ መጠን እንደ አዲስ አበባ ምክር ቤት ትኩረት በመስጠት እየተሰራበት እንደሆነና ወደፊትም ቼክሊስት ላይ ማካተት እንደሚገባ የጠቀሱት በአዲስ አበባ ምክርቤት የሕግና ፍትህ አስተዳደር ዘርፍ ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ሙሉነህ ደሳለኝ ሲሆኑ በትብብር ጥምረቱ ላይ ኃላፊነታቸውን የማይወጡ እና በትክክል እየተገበሩ ያሉትን መለየት እንዳለባቸው አቅጣጫ ሰጥተዋል ::
በመጨረሻም በቤቱ ለተነሱት አስተያየት እና ጥያቄዎች የቋሚ ኮሚቴው ስብሳቢ እና የጽ/ቤት ኃላፊው ምላሽ በመስጠት መድረኩ ተጠናቋል ::
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.