በአዲስ አበበ ከተማ አስተዳደር ፍትህ ቢሮ በሰው...

image description
- ውስጥ Laws    0

በአዲስ አበበ ከተማ አስተዳደር ፍትህ ቢሮ በሰው የመነገድ ሰውን በህገወጥ መንገድ ድንበር ማሻገር ወንጀልን መከላከል ማስተባበሪያ  ጽ/ቤት የ2016 ዓ.ም አፈጻጸም እና  በ2017 እቅድ ላይ  ውይይት ተደርገ፡፡

በአዲስ አበበ ከተማ አስተዳደር ፍትህ ቢሮ በሰው የመነገድ ሰውን በህገወጥ መንገድ ድንበር ማሻገር ወንጀልን መከላከል ማስተባበሪያ  ጽ/ቤት የ2016 ዓ.ም አፈጻጸም እና  በ2017 እቅድ ላይ  ውይይት ተደርገ፡፡
ሐምሌ 13/2016 ዓ. ም 
በመድረኩን የፍትህ ሚኒስተር የስራ  ሃላፊዎች ፣የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትህ ቢሮ ሃላፊዎች ፣የፍትህ ቢሮ የጽ/ቤት ሃላፊዎች ዳይሬክተሮች  ፣ የክፍለ ከተማ ፍትህ ጽ/ቤት ሃላፊዎች ፣የአዲስ አበባ  ፖሊስ ኮሚሽን፣ ፕላን ልማት ቢሮ፣ የስራና ክህሎት ቢሮ ፣  እንዲሁም መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች አመራሮች  ተገኝተዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትህ ቢሮ ምክትል ሃላፊ አቶ አስፋ መብራቴ  የመክፈቻ ንግግራቸው ህገወጥ የሰዎች ዝውውር አለም አቀፋዊ ይዘት ያለው አጀንዳ መሆኑን ገልጸው በሃገራችን ደግሞ አስከፊ ገጽታ ያለው የሃገርን ክብር የሚያጎድል በዜጎችም ላይ በስነልቦናቸው እና በአካላቸውም ላይ ከፍተኛ ተጽኖ ያሳደረ የህይወት ዋጋ እያስከፈለ ያለ ጉዳይ ነው ብለዋል።
ኃላፊው አክለውም የከተማ አስተዳደራችን    ወንጀሉን ለመከላከል የሚያሥችል ጠንካራ ተቋማዊ አደረጃጀት በመዘርጋት ምክር ቤት በማቋቋም አገልገሎት እየሰጠ መሆኑን ገልፀው ለማስተባበርያ ጽ/ቤቱ እና ወንጀሉን ለመከላከል እየሰሩ ላሉ መንግስታዊ ላልሆኑ ድርጅቶች ምስጋና አቅርበዋል፡፡ 
 
በሌላ በኩል በአዲስ አበባ ከተማ ፍትህ ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ተስፋዬ ደጀኔ በሰው የመነገድ ወንጀል  የሚፈፀመው እጅግ በረቀቀ እና በተወሳሰበ መንገድ ሲሆን በማህበረሰባችንም ላይ ከፍተኛ ማህበራዊ ፣ ኢኮኖሚያዊ ፣ ፖለቲካዊ ቀውስ  ከማምጣቱም  በላይ  በሰዎች  ላይ  ስነልቦናዊ  ጫና  ያመጣል ብለዋል። ቢሮው የችግሩን ውስብስብነት በመገንዘብ በቅንጅት መስራት ለማስቻል   በትብብር እና በጥምርት  ማደራጀት በዚህም አመርቂ ውጤት ታይቷል በማለት ከተማችን የህገወጥ የሠዎች ዝውውር መነሻ ፣ መተላለፊያ በመሆኗ ጫናው ስለሚበዛ ልዩ ክትትል በማስፈለጉ ሁሉም የበኩሉን ሊወጣ ያስፈልጋል ብለዋል ።
በእለቱ በሰው የመነገድ ጽ/ቤት ሃላፊው  አቶ ታደሰ ፈይሳ ህገወጥ የሰዎች ዝውውር ወንጀል  ውስብስብ እና የረቀቀ  በመሆኑን በአንድ ተቋም ብቻ በመስራት ውጤታማ መሆን ስለማይቻል እና የጋራ ትኩረት የሚፈልግ በመሆኑ  መንግስታዊ እና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችን በማሳተፍ በበጀት አመቱ የተሻለ አፈፃፀም ማምጣት ተችሏል ብለዋል። 
በመድረኩ በ2016 በጀት ዓመት በትብብር ጥምረቱ ወንጀሉን ለመከላከል እየተሰሩ ያሉ ስራዎችን  በአዲስ አበባ ፍትህ ቢሮ በሰው የመነገድ ሰውን በህገወጥ መንገድ ድንበር ማሻገር ወንጀል ለመከላከል ጽ/ቤት በበጀት አመቱ በተከናወኑ አበይት ተግባራቶች እና የ2017 ዕቅድ ያቀረቡ ሲሆን  ፤ በተጨማም የስራና ክህሎት ቢሮ፣ save the children እና hope for justice የተባሉት ግብረ ሰናይ ድርጅቶች በሕገ ወጥ የሠዎች ዝውውር ለመከላከል የተሰሩ ስራዎችን ላይ ከስደት ተመላሾችን መልሶ ስለማቋቋም፣ ከስደት ተመላሺ አቅም ስለመገንባት ፣ የሰራ እድል ስለመፍጠር ተመላሾችን  ቤተሰቦቻቸው  ጋር መቀላቅል አስመልክቶ የተሰሩ ስራዎችን ዘርዝረው  አቅርበዋል::      

በመጨረሻም የከተማ የስራ ቡድኖችን የስራ ክህሎት ቢሮ ፣የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ተሸላሚ ነበሩ እንድሁም  የክ/ከተማ ፍትህ ጽ/ቤት  አቃቂ ፣ ንፋስ ስልክ ላፍቶ እና ለሚኩራ እና ኮልፊ ክፍለ ከተሞች ከ1-3 ደረጃ ለወጡ  እውቅና የተሰጣቸው ሲሆን እንዲሁም በትብብር ጥምረት በጋራ ለሰሩ አለማቀፍ የፍልሰተኞች ድርጅት IOM ፣ freedom fund ፣አጋር ኢትዮጵያ ፣ህይወት ኢትዮጵያ ፣ CVM  Ethiopia ፣ MCDP፣ hope for justice፤የአዲስ አበባ ሴቶች ማህበር ፣ አለም አቀፍ  ህፃናት አድን ድርጅት save the children ለተባሉ ድርጅቶች እውቅና ተሰጥቷል ።


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.