የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትህ ቢሮ የጳጉ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትህ ቢሮ የጳጉሜ ቀናትን ማክበር ጀምሯል ፡፡

ጳጉሜ 1 ቀን 2016 ዓ.ም

“ የመሻገር ቀን ” በሚል ስያሜ እንደሀገር እየተከበረ ያለው በቢሮአችን በደማቅ ሁኔታ እየተከበረ ይገኛል፡፡

በቢሮው የመሻገር ቀንን አስመልክቶ በተለያየ ደረጃ ያሉ አመራሮችና ፈጻሚዎች በተገኙበት በ2016 በጀት ዓመት በተገኙ ዋና ዋና ድሎችና መሻገር በሚገባ አበይት ጉዳዮች ላይ ውይይት አካሂዷል፡፡

በወቅቱ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የፍትህ ቢሮ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ግርማ ወርቁ እንዳሉት አሮጌው አመት አልቆ አዲሱን ዓመት የምንሻገርበት ለጳጉሜ ወር በሰላም አደረሳችሁ ብለው ዕለቱን ስናከብር የተጠናቀቀው ዓመት ስኬቶችን ያስመዘገብንበት በሂደቱም አመርቂ ድሎችን ያገኘንበት እና የገጠሙን ተግዳሮቶች ደግሞ በአግባቡ የተወጣንበት ዓመት ነው ብለዋል፡፡

ኃላፊው አክለውም በቀጣይ ያገኘናቸውን ድሎች ወደ ላቀ ደረጃ በማድረስ በሀገርም ሆነ በከተማ ደረጃ የተጀመረውን ለውጥ በማገዝ ቢሮአችንን ወደፊት ማውጣት ይኖርብናል ብለዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትህ ቢሮ የሰው ሀብት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት ወ/ሮ ተናኜ ሸፈራው መልካም ምኞታቸውን በመግለፅ ሁሉም አመራርና ሰራተኛ በቅንጅት በመስራት አመቱን በውጤት ማጠናቀቅ ተችሏል በቀጣይም በመተባበር የቢሮውን ተልዕኮ ለማስፈፀም እርስ በርስ መመሰጋገን ያስፈልጋል ብለዋል፡፡


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.