"ሪፎርም ለላቀ አገልግሎት"በሚል መሪ ቃል ፍትህ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

"ሪፎርም ለላቀ አገልግሎት"በሚል መሪ ቃል ፍትህ ቢሮ በስራ ተከብሮ ውሏል፡፡

ጳጉሜ 2 የሪፎርም ቀን

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትህ ቢሮ ጳጉሜ 2 የሪፎርም ቀን አስመልክቶ አመራሩ እና  መላው የቢሮ ሰራተኞችአገልግሎት በመስጠት ጎን ለጎን  በተለያዩ ደማቅ ሁነቶች ቀኑን ሲያከብር ውሏል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትህ ቢሮ ኃላፊ አቶ ተክሌ በዛብህ የሪፎርም ቀንን አስመልክተው ውጤታማና ተደራሽ የሆነ የመንግስት አገልግሎት በመስጠት ቢሮው ሀላፊነቱን እየተወጣ ይገኛል፡፡ ለዚህም ደግሞ ሁላችሁም የድርሻችሁን ተወጥታችኃል በማለት እንኳን ለሪፎርም ቀን አደረሳችሁ ብለዋል ቢሮው ውጤታማ የሆነ የአገልግሎት አሰጣጥ በከተማ እንዲኖር መጠነ ሰፊ ስራዎችን እየሰራ ይገኛል እንደተቋም ሪፎርሙን አስመልክቶ የአሰራር ማሻሻያ፣ የህግ ማዕቀፎችን ፣ አደረጃጀቶችን እንዲሁም ምቹ የስራ ሁኔታን ከመፍጠር አኳያ ሪፎርም እያደረገ ይገኛል ፤ በዚህም በባለፈው አመት ውጤታማ  በመሆን እውቅና ተችሮታል በማለት ገልፀዋል፡፡

ኃላፊው አክለውም ሪፎርም ቀንን ስናከብር የመጣንበት ሂደት  የምንዘክርበት ብቻ ሳይሆን መጪውንም በማቀድ ለተሻለ ስራ የምንዘጋጅበት ነው በማለት አዲሱ አመት ውጤታማና ፍሬያማ የምንሆንበት አመት እንዲሆን በማኔጅመንቱ ስም መልካም ምኞቴን እገልጻለው ብለዋል፡፡

"የላቀ አገልግሎት ልንሰጥ የምችለው ሪፎርም መሰረት ያደረገ ስራ ስንሰራ ነው" ያሉት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትህ ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ አሰፋ መብራቴ ሲሆኑ ሪፎርም ስራ ከማብቃት ይጀምራል ሰራተኛው በአንድም በሌላ መንገድ ራስን ብቁ ማድረግ ይኖርበታል በማለት የተቋም የአሰራር ስርአትን፣ አደረጃጀትን እና የአቅም ግንባታ በማድረግ አገልግሎት አሰጣጡን ማሻሻል ሲሆን ቢሮው በ2016 በጀት አመት ይህን ተግባር ሲፈፅም ቆይቷል በመሆኑም ሪፎርምን በመደገፍ ሁሉም የድርሻውን ሊወጣ ይገባል ብለዋል፡፡

የሪፎርም ቀን አስመልክቶ የቢሮው ማኔጅመንት አባላት የጽ/ቤቶችን እና የዳይሬክቶሬቶችን አገልግሎት አሰጣጥ ተዘዋውረው ተመልክተዋል፡፡ በመጨረሻም እለቱን አስመልክቶ የተለያዩ ሁነቶች ተከናውኖ በደማቅ ሁኔታ ተከብሮ ውሏል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትህ ቢሮ

ኮሚውንኬሽን ዳይሬክቶሬት


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.