በፍትህ ቢሮ  እና በበአዲስ አበባ አመራር አካዳ...

image description
- ውስጥ Laws    0

በፍትህ ቢሮ  እና በበአዲስ አበባ አመራር አካዳሚ ለማዕከል እና ለክፍለከተማ አመራሮች እና ለሁሉም ለማእከል እና ክፍለከተማ ዓቃቢያነህግ ሲሰጥ የነበረው የአቅም ግንባታ ስልጠና የመጀመሪያው ዙር ዛሬ ተጠናቋል ።

በፍትህ ቢሮ  እና በበአዲስ አበባ አመራር አካዳሚ ለማዕከል እና ለክፍለከተማ አመራሮች እና ለሁሉም ለማእከል እና ክፍለከተማ ዓቃቢያነህግ ሲሰጥ የነበረው የአቅም ግንባታ ስልጠና የመጀመሪያው ዙር ዛሬ ተጠናቋል ።

የአቅም ግንባታ ስልጠና በኮንስትራክሽን ህግ ፣በዓቃቢያነ ህግ ስነምግባር እና በመሬት እና መሬት ነክ ህግ ዙሪያ ለሶስት ተከታታይ ቀናት ሲሰጥ መቆየቱ  ተገልጿል።

ዛሬ በመሬት እና መሬት ነክ ጉዳዮች ህግ ዙሪያ በፍትህ ቢሮ የህግ ማርቀቅ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር በሆኑት አቶ ጀማል ሳላህ ሰፊ ማብራሪያ የያዘ ሰነድ ያቀረቡ ሲሆን በስልጠናቸው በደንብ ቁጥር 162/2016 እና 163/2016 ድንጋጌዎችን መሰረት በማድረግ በዚህ ደንብ በተሻሩ ህጎች ላይ ያልነበሩ እና አዳዲስ ድንጋጌዎችን እና ማሻሻያ የተደረገባቸው ድንጋጌዎችን ማዕከል በማድረግ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጥተዋል።

ስልጠና ወቅቱን ያገናዘበ ከተሰጣቸው ተግባር ጋር የተገናዘበ እና ለስራቸው እጅግ አጋዥ መሆኑን ዐቃቢያነ ህግ ገልጸው በቀጣይ ቢሮው መሰል ስልጠናዎችን በተለይ በኮንስትራክሽን ህግ ዙሪያ ሰፋ ያለ ጊዜ በመስጠት ቢያዘጋጅ የሚል ሃሳብ ሰጥቷል።

በፍትህ ቢሮ ጉባኤ ጽ/ቤት ኃላፊ የሆኑት አቶ አብይ አስናቀ የመጀመሪያውን ዙር ስልጠና ማጠቃለያ ንግግር ባደረጉበት ወቅት ሁሉም ሰልጣኝ ለስልጠናው ትኩረት በመስጠት በጥብቅ ዲሲፕሊን ስለተከታተላችሁ ከልብ አመሰግናለሁ በማለት ሁም ዐቃብያነ ህግ ስልጠናውን በስራ ማሳየት እንደሚጠበቅ አሳስበዋል።

ኃላፊው አክለው ስልጠናው ሁለተኛው ዙር መስከረም 10 ቀን 2017 ከዘጠኝ ሰአት ጀምሮ እንደሚቀጥል ገልጸው ሁሉም የሚመለከተው ዐቃቢያነህግ በተገለጸው ቦታና ሰዓት እንዲገኝ አሳስበዋል።


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.